የዓለማችን ተወዳጅ 10 ስሞች
ሙሃመድ፣ ኖህ እና ሶፊያ የወቅቱ ተወዳጅ የህጻናት ስሞች ተብለዋል

በመላው ዓለም ልጆችን በዝነኛ ሰዎች ስም መሰየም እየተለመደ መጥቷል
ስም ከማህበራዊ ማንነት መገለጫዎች መካከል አንዱ ሲሆን ወላጆች ልጆቻቸውን ከማንነታቸው ጋር ተያያዥ የሆኑ እና ትርጉም የሚሰጡ ስሞችን ይሰጣሉ፡፡
የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች ወይም ሶሺዮሎጅስቶች እንደሚሉት ወላጆች የልጆቻቸውን ስም ለማውጣት ሀይማኖትን፣ ክስተቶችን አልያም እንደ አርአያ የሚያዩትን ሰው መሰረት በማድረግ ስም ይሰይማሉ፡
ከወላጆች እና ህጻናት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን በማውጣት የሚታወቀው ፓረንትስ ዶት ኮም የተሰኘው ድረገጽ እንዳስነበበው ከሆነ ሙሃመድ በአሁኑ ወቅት በብዛት ህጻናት የሚጠሩበት ቀዳሚው ስም ሆኗል፡፡
ኖህ፣ሶፊያ እና ሊያም ከሁለተኛ እስከ ሶስተኛ ድረስ ያሉ ስሞች ሆነዋል፡፡ በብሪታንያ ሙሀመድ የሚለው ስም ቀዳሚ ሲሆን በአሜሪካ ደግሞ ኦሊቨር እና ኦሊቪያ የተሰኙት ስሞች ቁጥር አንድ ተብለዋል፡፡
በታዋቂ ሰዎች ስም የሚጠሩ ህጻናት ቁጥር እያደገ ነው የተባለ ሲሆን በተለይም ሚሌይ፣ኤንድሪክ ፣ ሮቢ፣ ሪሀና ፣ ኤሊሽ፣ ላና እና ኤልተን ስሞች ዋነኞቹ ሆነዋል፡፡