በቲክቶክ በርካታ ተከታዮችን ያፈሩ ግለሰቦች
ጣሊያናዊው ካቢ ሌም በቲክቶክ ከ161 ሚሊየን ተከታዮችን በማፍራትና ከማህበራዊ ትስስር ገጹ ሚሊየን ዶላሮችን በማግኘት ቀዳሚው ነው
የቻይናው ባይትዳንስ ኩባንያ ንብረት የሆነው ቲክቶክ ከ2 ቢሊየን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት
በፈረንጆቹ 2016 በይፋ የተዋወቀው ቲክቶክ በአጭር ጊዜ ተወዳጅነትን ያተረፈ የአጫጭር ተንቀሳቃሽ ምስሎች ማጋሪያ ነው።
በመላው አለም ከ2 ቢሊየን በላይ ደንበኞችን ያፈራው ቲክቶክ በ2022 ሰዎች በቀን በአማካይ ለ95 ደቂቃ የሚጠቀሙት ማህበራዊ ትስስር ገጽ እስከመሆን ደርሷል።
የቪዲዮ መተግበሪያው በመስከረም ወር 2022 ብቻ ከፕሌይ ስቶር 24 ሚሊየን ጊዜ በመውረድም በበርካታ የአንድሮይድ ስልክ ተጠቃሚዎች የተጫነ መተግበሪያ ለመሆን መብቃቱ ይታወሳል።
ከ150 ሚሊየን በላይ የቲክቶክ ተጠቃሚዎች ያሉባትና በርካታ ዜጎቿ መተግበሪያውን በመጠቀም ከሀገራት መሪ ናት፤ ኢንዶኔዥያ በ126 ሚሊየን ትከተላለች።
አሜሪካ የቻይናውን ባይትዳንስ ኩባንያ ንብረት ለማገድ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የፈረሙበት ህግ ያወጣች ሲሆን፥ ኩባንያው ድርሻውን ለአሜሪካውያን እንዲሸጥ ቀነ ገደብ አስቀምጣለች።
ለበርካቶች ራስን ማስተዋወቂያና ስራ መፍጠሪያ መድረክ የሆነውን ቲክቶክ እንደ ጣሊያናዊው ካቢ ሌም የተጠቀመበት የለም።
እስከ መጋቢት 2024 161.4 ሚሊየን ተከታይ ያለው ካቢ ለተለያዩ ታዋቂ ኩባንያዎች ማስታወቂያዎችን በመስራት ሚሊየን ዶላሮችን አግኝቷል።
በቲክቶክ በርካታ ተከታዮችን ያፈሩ ግለሰቦችን ዝርዝር ይመልከቱ፦