በሳይበር ደህንነት ስጋትና ብሄራዊ የደህንነት ስጋት ሀገራት እንደ ምክንያት ያስቀምጣሉ
በፈረንጆቹ 2016 ላይ በቻይና የተሰራው ቲክቶክ የማህበራዊ ትስስር ገጽ በጥቂት ዓመታት ውስጥ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ደንበኞችን ማፍራት ችሏል።
ይህ መተግበሪያ አጫጭር ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በአጭር ጊዜ ለብዙዎች እንዲደርስ ማድረግ የሚያስችል ሲሆን ለብዙዎችም የገቢ ምንጭ ሆኗል።
ይህ ፈጣን መተግበሪያ በቻይና መሰራቱን ተከትሎ ምዕራባዊያን ሀገራት በጥርጣሬ የሚያዩት ሲሆን በተለይም አሜሪካ በዚህ መተግበሪያ ላይ እምነት እንደሌላት ስትናገር ቆይታለች።
በርካታ ሀገራትም በሳይበር ደህንነት ስጋት፣ ተገቢ ያልሆኑ ይዘቶችን በማሰራጨትና ብሄራዊ የደህንነት ስጋትን እንደ ምክንያት በማስቀመጥ በማገድ ላይ ይገኛሉ።