ፓስወርድን በሚገባ ጠብቀው የሚያስቀምጡ 10 መተግበሪያዎች
መተግበሪያዎቹ በርካታ የይለፍ ቃላትን በአንድ ቦታ ለማስቀመጥና የማይሰበሩ የይለፍ ቃላትን ለማግኘት ያግዛሉ
በቀላሉ የሚገመቱ የይለፍ ቃላትን የመጠቀም ልማድ አሁንም ለመረጃ መንታፊዎች እድል መፍጠሩ ይነገራል
ለተለያዩ አካውንቶች የምንጠቀማቸው ሚስጢራዊ የይለፍ ቃላት (ፓስወርዶች) መመሳሰል እና በቀላሉ ተገማች መሆን የሳይበር ጥቃት ፈጻሚዎችን ስራ እንዳቀለለላቸው ይነገራል።
ከ800 ሚሊየን በላይ በመረጃ መንታፊዎች እጅ የወደቁ የይለፍ ቃላት ላይ ጥናት ያደረገው ስፔኮሶፍት የተባለ ተቋም እንደሚለው፥ 88 ከመቶው የይለፍ ቃላት ከ12 ፊደላት ወይም ቁጥሮች ያነሱ ሆነው ተገኝተዋል።
ለተለያዩ የኢሜል እና ማህበራዊ ትስስር ገጾች አንድ አይነት የይለፍ ቃል መጠቀምም ሌላኛው ችግር ሆኖ የቀጠለ ጉዳይ ነው ይላል ስፔኮሶፍት።
ውስብስብና የተለያዩ የይለፍ ቃላትን ከመጠቀም ይልቅ ላለመርሳት በሚል ተመሳሳይ ፓስወርዶችን መጠቀም በስፋት ይስተዋላል።
ለዚህም በአንድ ቋት የይለፍ ቃላትን መመዝገብ የሚያስችሉ መተግበሪያዎች ተሰርተዋል።
መተግበሪያዎቹ የይለፍ ቃላትን በመርሳት የሚመጡ ችግሮችን ከማስቀረት ባሻገር ለእያንዳንዱ አካውንት ለመስበር የሚከብዱ ፓስወርዶችን በማቅረብም ይታወቃሉ።
በይለፍ ቃላት መጠበቂያ መተግበሪያዎቹ እንደ ክሬዲት ካርድ ቁጥር ያሉና ሌሎች ሚስጢራዊ መረጃዎችን ለማስቀመጥም ይረዳሉ ነው የተባለው።
በርግጥ አንዳንድ የይለፍ ቃላት መጠበቂያ ተብለው የሚቀርቡ መተግበሪያዎች በራሳቸው መረጃ መመንተፊያ ሆነው እንደሚያገለግሉ ተደርሶበታል።
“ላስትፓስ” የተሰኘ መተግበሪያ በ2022 የይለፍ ቃላትን ደህንነት አስጠብቃለሁ ብሎ የበርካቶችን የይለፍ ቃል አደጋ ላይ መጣሉም ለዚህ በአብነት ይነሳል።
ቀጥለው የተዘረዘሩት 10 መተግበሪያዎች ግን የይለፍ ቃላትን ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ አስተማማኝነታቸው መረጋገጡን በሲኔት ኒውስ ዘግቧል።
1. ኖርድ ፖስ (NordPass)
2. ሮቦፎርም (RoboForm)
3. ዋንፖስወርድ (1Password)
4. ኪፐር(Keeper)
5. ዳሽሌን (Dashlane)
6. ላስትፖስ(LastPass)
7. ፖስዋርደን (Passwarden)
8. ስቲኪይፖስዎርድ (Sticky Password)
9. ኢንፖስ(Enpass)
10. ቢትዋርደን (Bitwarden)