በርካታ ዜጎቻቸው በከፍተኛ ጭንቀት የሚኖሩባቸው የአፍሪካ ሀገራት
በአፍሪካ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት እና የኢኮኖሚ ሁኔታ ለሰዎች ጭንቀት ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው
ደቡብ ሱዳን በከፍተኛ ጭንቀት በሚኖሩ ዜጎች ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሆናለች
የጭንቀት ደረጃው ቢለያይም የሰው ልጅ በህይወት ጉዞው በጭንቀት የሚገፋው ጊዜ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡
የጭንቀት መለኪያ መስፈርቶች እንደየ ሀገራቱ እና እንደየ አካባቢው የተለያየ ሲሆን በአፍሪካ ሰዎችን በአብዘሀኛው የሚያስጨንቁ ምክንያቶች መሰረታዊ የሚባሉ ጉዳዮች መሆናቸውን ሲኢኦ ዎርልድ መጽሄት አስነብቧል፡፡
በአፍሪካ ዋነኛ የጭንቀት መነሻ ተብለው የተዘረዘሩ ምክንያቶች የፖለቲካ አለመረጋጋት ፣ የሰላም እጦት ፣ የኑሮውድነት ፣ የስራ አጥነት እና ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች ናቸው፡፡
አፍሪካዊያን በእነዚህ እና በተያያዥ ጉዳዮች የተነሳ በሀገራቸው እና በነጋቸው ላይ እርግጠኞች ባለመሆናቸው በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ኑሯቸውን ይገፋሉ ተብሏል፡፡
የ211 ሀገራትን የጭንቀት ደረጃ ያወጣው ሲኢኦ ዎርልድ መጽሄት ከገንዘብ ጋር በተገናኝ ፣ በፖለቲካ አለመረጋጋት ፣ በኢኮኖሚ እና በጤና ሁኔታዎች የሚፈጠሩ ጭንቀቶች በሚል በከፋፈላቸው መስፈርቶች የአፍሪካ አህጉር ደረጃ ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በሪፖርቱ ደቡብ ሱዳን ቀዳሚ ስትሆን ብሩንዲ እና ዲአር ኮንጎ በቅደም ተከተል ይከተላሉ፡፡