ልዩልዩ
ብዙ ተመልካቾ ያገኙ የዓለም ሙዚቃ ክሊፖች የትኞቹ ናቸው?
ከሰባት ዓመት በፊት የወጣው በስፓኒሽ ቋንቋ የተዘፈነው ዴስፓሲቶ ሙዚቃ በተመልካች ብዛት ቀዳሚው ሆኗል
የኤድ ሺራን እና ዊዝ ካሊፋ ሙዚቃዎች በተመልካች ብዛት ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃዎችን የያዙ ሙዚቃዎች ናቸው
ብዙ ተመልካቾ ያገኙ የዓለም ሙዚቃ ክሊፖች የትኞቹ ናቸው?
ዩቲዩብ በመላው ዓለም የሙዚቃ ስራዎች ከሚቀርብባቸው መንገዶች መካከል አንዱ ሲሆን በልዊስ ፎንሲ የተዘጋጀው ዴስፓሲቶ የሙዚቃ ክሊፕ እስካሁን በ8 ነጥብ 4 ቢሊዮን ተመልካቾች ብዛት ቀዳሚው ሆኗል፡፡
በሁለተኛነት ደግሞ ኤድ ሺራን የተቀነቀነው ሼፕ ኦፍ ዩ የተሰኘው ሙዚቃ 6 ነጥብ 2 ቢሊዮን ጊዜ የታየ ሲሆን ሲ ዩ አጌን የተሰኘው የዊዝ ካሊፋ ሙዚቃ ደግሞ 6 ነጥብ 1 ቢሊዮን ጊዜ እይታ በማግኘት ሶተኛሙ የሙዚቃ ስራ ነው፡፡
የብሩኖ ማርሱ አፕታወን ፈንክ የተሰኘው ሙዚቃ ደግሞ 5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ጊዜ በመታየት አራተኛው ሲሆን የደቡብ ኮሪያው ጋንግናም ስታይል ደግሞ 5 ቢሊዮን ጊዜ በመታየት አምስተኛው ተወዳጅ የሙዚቃ ስራ ሆኗል፡፡