ሁለት ማህፀን ያላት እናት በሁለት ቀናት ውስጥ ሁለት ልጆችን ወለደች
የ32 ዓመቷ ኬልሲ ሃትቸር ማክሰኞ አንድ ሴት ልጅ ወለደች፣ ሁለተኛዋን ደግሞ ረቡዕ እለት ወልዳለች
ከ1 ሚሊየን በአንዷ የሚፈጠር አስገራሚው ክስተት እናት 20 ሰዓታትን በምጥ አሳልፋለች
በአሜሪካዋ አላባማ ሁለት ማህፀን ያላት እናት በሁለት ቀናት ውስጥ ሁለት ልጆችን ወለደች።
ከአንድ ሚሊዮን እርግዝና በአንድ እናት ላይ በሚከሰተው በዚህ በሁለት ማህጸን እርግዝና፤ እናት 20 ሰዓታትን በምጥ አሳልፋለች ነው የተባለው።
የ32 ዓመቷ ኬልሲ ሃትቸር ማክሰኞ የመጀመሪያዋን ሴት ልጅ ወለደች፣ ሁለተኛዋን ደግሞ ረቡዕ እለት በአላባማ ዩኒቨርሲቲ በበርሚንግሃም ሆስፒታል በሰላም ተገላግላለች።
እናት ኬልሲ ሃትቸር በማህበራዊ ትስስር ገጿ ላይ ተዓምርኞቹ ስትል የጠራቻቸው ልጀቿ ቤተሰቧን መቀላቀላቸወውን ያታወቀቸወ ሲሆን፤ የህክምና ባለሙያዎችን "አስደናቂ" በማለት አሞካሽታለች።
በሁለቱም ማህጸን ማርገዝ ማለት በቀላሉ ሁለት የተለያየ እርግዝና ተከስቷል እንደማለት ነው የሚሉት የሃቸርን እርግዝና የሚከታተሉት ዶክተር ሪቻርድ ዴቪስ፥ በዚህም ጽንሶቹን መንትያ ማለት እንደሚያስቸግር ይናገራሉ።
በአላባማ ነዋሪ የሆነችው ኬስሊ ሃቸር ከ17 አመቷ ጀምሮ ሁለት ማህጸን እንዳላት የወቀች ሲሆን፤ በአላባማ ዩኒቨርሲቲ በበርሚንግሃም ሆስፒታል እንዲህ አይነት ክስተት 0.3 በመቶ ሴቶች ላይ ሊከሰት እንደሚችል አስታውቋል።
እንደ ሃቸር ሁለት ማህጸን ኖሯቸው ሊፈጠሩ የሚችሉት ከ1 ሺህ ሴቶች ሶስቱ ብቻ ናቸው።
በሁለቱም ማህጸን የመጸነስ እድሉም ከ1 ሚሊየን ሴቶች በአንደኛዋ ይሳካል ተብሎ እንደመታመንም በአላባማ ዩኒቨርሲቲ በበርሚንግሃም ሆስፒታል ገልጿል።