በ2021ም ኢንዶኔዥያዊት እንስት ከነፋስ ጸነስኩ ማለቷ የሚታወስ ነው
በደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ኮሎምቢያ ከነድንግልናዬ እርጉዝ ሆኔ ተገኘሁ” የሚል አስተያየት መስጠቷ መነጋገሪያ ሆኗል።
“ከወንድ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አልፈጸምኩም ያለችው” የ19 አመት ወጣት ከማላምቦ ቴሌቬዥን ጋር ባደረገችው ቆይታ ነው አስገራሚውን ክስተት ያጋራችው።
ስሟ ያልተጠቀሰው እንስት “ምድራዊ ባልሆነ ሃይል” መጸነሷን ገልጻለች።
የተለየ ህልም መመልከቷንና በክፍሏ ውስጥ “መንፈስ” እንደተገኘ ካመነችበት እለት በኋላ የወር አበባዋ መቅረቱንም ትናገራለች።
ጉዳዩ አሳሳቢ እየሆነ ሲመጣም ከእናቷ ጋር በመሆን ወደ ህክምና ተቋም ስታመራ መጸነሷ መረጋገጡን ነው ያስረዳችው።
“ከአንድም ወንድ ጋር አንሶላ አልተጋፈፍኩም፤ የወር አበባዬ ቆሞ ወደ ህክምና ተቋም ከሄድኩ በኋላ መጸነሴን አረጋገጥኩ” ስትልም ታስረግጣለች።
ጉዳዩ ለእርሷም ቢሆን የተለየና ለማመን የሚከብድ ቢሆንም የሆነው ይሄው ነው ማለቷንም ኦዲቲ ሴንትራል አስነብቧል።
ወጣቷ በ”ድንግልና ጸነስኩ” የማለቷ ዜና ከተሰማ በኋላም በማህበራዊ ሚዲያዎች የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው።
በርካቶቹ ለማመን የሚከብድ ጉዳይ ነው፤ ቤተሰቦቿ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ እንዳለች እንዳያውቁ ስለፈለገች ነው ያሉ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ ተመሳሳይ አጋጣሚዎች እንዳሉ ሰምተናል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።