የአሚሶም ጦር ዋና አዛዥ የነበሩት ሜጀር ጀነራል ናባሳ አዲሱ ኡጋንዳ ፖሊስ አዛዥ ሆነዋል
ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ የፖሊስ አዛዡን ከስልጣን አነሱ።
ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሽብር ጥቃቶችን በማስተናገድ ላይ ስትሆን፤ ከሰሞኑ ደግሞ ተደጋጋሚ የሽብር ጥቃቶች ደርሰዋል።
በዚህም ምክንያት ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ የሀገሪቱን ፖሊስ አዛዥ ከስልጣን ማንሳታቸውን ሲ.ጂ.ቲ.ኤን አፍሪካ ዘግቧል።
ኡጋንዳ ፖሊስን በአዛዥነት ሲመሩ የነበሩት ብርጋዴር ጀነራል ኬቲ ካቱንጊ በሜጀር ጀነራል ናባሳ እንደሚተኩ ዘገባው አክሏል።
ሜጀር ጀነራል ናባሳ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ጦር ወይም አሚሶም ጦር ዋና አዛዥ በመሆን አገልግለዋል።
በኡጋንዳ የሽብር ድርጊቶች እየጨመሩ የመጡ ሲሆን ከሁለት ወር በፊት በአገሪቱ መከላከያ ሚኒሠትር ላይ በተፈጸመ የግድያ ሙከራ የሚኒስትሩ ስት ልጅ ሐይወቷ ያለፈ ሲሆን ባሳለፍነው እሁድ እለትም በተፈጸመ የሽብር ጥቃት አንድ ሰው ሲሞት ሶስት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።