
የኖቤል ሽልማት ያሸነፉት እና በፈረንጆቹ 2021 በመፍንቅለ መንግስት ከስልጣን ከመወገዳቸው በፊት ሱ ኪ ምያንማርን ለ5 አመታት መርተዋል
በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተነሱት የማያንማሯ መሪ ሱ ኪ በሙስና ወንጅል ጥፋተኛ ተብለው የ 5 አመት እስራት ተፈርዶባቸውል፡፡
ፍርድ ቤቱ በሱ ኪ ላይ የጥፋተኝነት ብይን ያስተላለፈው ሱ ኪ ከተከሰሱባቸው 11 የሙስና ወንጀሎች በመጀመሪያው ጥፋተኛ በመሆናቸው መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የኖቤል ሽልማት ያሸነፉት እና በፈረንጆቹ 2021 በመፍንቅለ መንግስት ከስልጣን ከመወገዳቸው በፊት ምያንማርን ለ5 አመታት መርተዋል፡፡ሱ ኪ በተከሰሱባቸው ክሶች ጥፋተኛ የሚባሉ ከሆነ 190 አመት እስር ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡
ሮይተርስ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገን ምንጭ ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ፍርዱ የተላለፈው ዳኛው እንደገቡ ብዙም ሳይቆዩ የተላለፈ መሆኑ፤ ውሳኔ አስቀድሞ የተላለፈ ነው የሚል ትችትን አስነስቷል፡፡
በምያንማር ወደታራዊ አምባገነንን በመቃወም የምትታወቀው የ76 አመቷ ሱ ኪ የእስር ጊዜዋን ወደምታሳልፍበት ቦታ መዛወሯ ግልጽ አልሆነም፡፡
ሱ ኪ ከታሰረች ጀምሮ ባልታወቀ ቦታ የታሰረችበት ቦታ ወታደራዊው አገዛዝ ይፋ አላደገም ነበር፡፡
በሱ ኪ ላይ የቀረበው የቅርብ ጊዜ ክስ፤ ሱ ኪ 11.4 ኪ ግ ወርቅን ጨምሮ 600 ሚሊዮን ዶላር ተቀብላለች በሚል ነው፤ ሱ ኪ ግን ክሱን የማይረባ ነው በሚል አትቀበለውም፡፡