ፖለቲካ
አሜሪካ ከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ በቻይና፣ በሰሜን ኮሪያና ምያንማር ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለች
ማዕቀቡ በሶሱቱ ሀገራት በሚገኙ ግለሰቦችና ተቋማትን ኢላማ ያደረገ ነው
ብሪታኒያና ካናዳም አሜሪካን ተከትለው በምያንማር ላይ ማዕቀብ ጥለዋል
አሜሪካ ከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ በቻይና፣ በሰሜን ኮሪያ፣ በምያንማር እና በባንግላዴሽ ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣሏ ተነግሯል።
አሜሪካ ማዕቀቡን የጣለችው በሀገራቱ ውስጥ ከሚፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር ግንኙነት አሏቸው ባለቻቸው ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ መሆኑም ተነግሯል።
“ሴንስታይም” የተባለው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ተቋምን ደግሞ በአሜሪካ ኢንቨስትመንት ጥቁር መዝገብ ዝርዝር ውስጥ ማስገባቷን ሮይተርስ ዘግቧል።
ብሪታኒያ እና ካናዳም ከሰባዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ አሜሪካን በመከተል በምያንማር ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣላቸው ተሰምቷል።
በሰሜን ኮሪያ ላይ ማዕቀብ ሲጣል በፕሬዚዳንት ባይደን ዘመን ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የተባለ ሲሆን፤ በማይናማር ላይ የተጣለው ማዕቀብም የሀገሪቱ ጦር ተቋማትን ኢላማ ያደረገ መሆኑ ተነግሯል።
የሰሜን ኮሪያ የተመድ ልዩ መልእከተኛም ይሁን በአሜሪካ የሚገኙ የቻይና፣ የባንግላዴሽ እና ምያንማር ኤምባሲዎች በማእቀቡ ዙሪያ እስካሁን አስተያየት አልሰጡም።