ሰሜን ኮሪያ በዉሃ ውስጥ ኑክሌር መሸከም የሚችል ድሮን ሙከራ አደረገች
በደቡብ ኮሪያ እና አጋሮቿ የምትበሳጨው ሰሜን ኮሪያ ለማስጠንቂያ ሚሳይል በማስወንጨፍ ላይ ትገኛለች
የድሮን ልምምዱ የአሜሪካ ቢ-1ቢ ስትራቴጂክ ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ለልምምድ ወደ ደቡብ ኮሪያ ባለፈው እሁድ መመለሷን ተከትሎ ነው
ሰሜን ኮሪያ በውሃ ውስጥ ኑክሌር የሚይዝ አዲስ ሰው አልባ አውሮፕላን መሞከሯን ሮይተርስ ሲል የሀገሪቱን የመንግስት የዜና ወኪል ኬሲኤንኤ ጠቅሶ ዘግቧል።
ጉልህ በሆነ መልኩ፣ ሰው አልባ አውሮፕላኑ ከውሃ በታች ለ59 ሰአታት ያለማቋረጥ መንቀሳቀሱንና ይህም የአሜሪካን እና የደቡብ ኮሪያን ታጣቂ ሃይሎችን ለማስፈራራት የተደረገ ልምምድ ነው ተብሏል።
የሰሜን ኮሪያ ጦር በዚህ ሳምንት በኪም ጆንግ ኡን በተመራው የውትድርና ልምምድ ወቅት አዲሱን የጦር መሳሪያ ስርዓት አሰማርቶ ሞክሯል፣ አላማውም አውዳሚ ፍንዳታ ማድረስ ይችል እንደሆነ ለመወሰን ነው።
ኬሲኤንኤ እንደዘገበው “ይህ የኑክሌር የውሃ ውስጥ ጥቃት ሰው አልባ ድሮን በማንኛውም የባህር ዳርቻ እና ወደብ ላይ ሊነሳ ወይም በገጸ ምድር መርከብ እየተጎተተ ሊንቀሳቀስ ይችላል።
እንደ ብዙ የሚዲያ ዘገባዎች፣ በፒዮንግያንግ የተሞከረችው የኑክሌር አቅም ያለው የውሃ ውስጥ ጥቃት ሰው አልባ አውሮፕላኖች “ራዲዮአክቲቭ ሱናሚ” ሊይዝ ይችላል።
ሰው አልባ አውሮፕላኑ ለሙከራው ማክሰኞ እለት በደቡብ ሃምዮንግ ግዛት አቅራቢያ ባለው ውቅያኖስ ውስጥ እንዲቀመጥ የተደረገ ሲሆን ለ59 ሰአታት ከ12 ደቂቃ ከ80 እስከ 150 ሜትሮች ጥልቀት (260 እስከ 490 ጫማ) ጥልቀት ላይ መንሳፈፍ ችሏል።
ይሁን እንጂ የደቡብ ኮሪያው የዜና ወኪል ዮንሃፕ የድሮኑ የመጨረሻ ኢላማ ነጥብ በሆንግዎን ቤይ ውሃ ላይ የተተከለው የማስመሰል የጠላት ወደብ ነው ብሏል።
የድሮን ልምምዱ የአሜሪካ ቢ-1ቢ ስትራቴጂክ ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ለወታደራዊ ልምምድ ወደ ደቡብ ኮሪያ ባለፈው እሁድ መመለሷን ተከትሎ ነው።
ደቡብ ኮሪያ እና አጋሮቿ በተደጋጋሚ በሚያደርጉት በሚያደርጉት ወታደራዊ ልምምድ የምትበሳጨው ሰሜን ኮሪያ ለማስጠንቂያ ሚሳይል በማስወንጨፍ ላይ ትገኛለች።