ሰሜን ኮሪያ ወደ 800ሺህ የሚጠጉ ዜጎቿ አሜሪካን ለመዋጋት መመዝገባቸውን አስታወቀች
ፒዮንጊያንግ ከአሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ የገባችው ውጥረት ቀጠናውን አንዳያተራምሰው ተስግቷል
የሀገሪቱ ወታደር ቤት ለመቀላቀል ፈቃደኛ ከሆኑት አብዛኞቹ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ናቸው ተብሏ
ሰሜን ኮሪያ፤ ወደ 800ሺህ የሚጠጉ ዜጎቿ “አሜሪካን ለመዋጋት” በፈቃደኝነት ለውትድርና መመዝገባቸውን አስታወቀች፡፡
የሀገሪቱ ወታደር ቤት ለመቀላቀል ፈቃደኛ ከሆኑት አብዛኞቹ ተማሪዎች እና ሰራተኞች መሆናቸውም የሀገሪቱ ሮዶንግ ሲንሙን ጋዜጣ ዘግቧል።
- ሰሜን ኮሪያ አሜሪካና ደቡብ ኮሪያን ለማስጠንቀቅ የተኮሰችው ህዋሰኦንግ-17 ሚሳዔል እውነታዎች
- ሰሜን ኮሪያ ማንኛውም የአሜሪካ ወታደራዊ እንቅቃሴ “የጦርነት አዋጅ” አድርጋ እንደምትቆጥር አሳሰበች
የሰሜን ኮሪያ ይህን ዜና የወፋ ያደረገችው ዋሽንግተን እና የሴኡል በአይነቱ ልዩ የሆነውን ወታደራዊ ልምምድ በማድረግ ላይ ባሉበት በአሁኑ ወቅት መሆኑ ነው፡፡
ፒዮንጊያንግ ከአሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ የገባችው ውጥረት ቀጠናውን አንዳያተራምሰው ተስግቷል፡፡
በተለይም ሰሜን ኮሪያ በተለያዩ ጊዜያት የምታስቀነጭፋቸው የሚሳይል ሙከራዎች ውጥረቱን እንዳያባብሰው የሚል የበርካቶች ስጋት ሆኗል፡፡
ሰሜን ኮሪያ፤ ሐሙስ እለት የሁዋሶንግ-17 አህጉር አቋራጭ ሚሳይል (አይሲቢኤም) ወደ ጃፓን ባህር ማስቀንጨፏ ይታወሳል፡፡
ሀገሪቱ ከፒዮንግያንግ አውሮፕላን ማረፊያ ያስወነጨፈቸው ሚሳይል የጋራ ልምምድ በማካሄድ ላይ ላሉት ዋሽንግተን እና ሴኡል ጠንካራ ምላሽ ለመስጠት ያለመ እንደሆነም ነበር የገለጸችው፡፡
ሚሳይሉን የማስቀንጨፍ መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ የሚያካሂዱት ጋራ ወታደራዊ ልምምዱድ በኮሪያ ልሳነ ምድር ያለውን ውጥረት የሚያባብስ ነው ሲሉ ከሰዋል፡፡
ያም ሆኖ የጠላትን ጥቃት ለመከላከል ሁሌም ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል ሲሉ ተደምጠዋል ፕሬዝዳንቱ፡
"ጠላቶችን እንዲበረግጉ በማድረግ እና ጦርነትን በመግታት እንዲሁም ህዝባችን ሰላማዊ ህይወት ኖሮት ለሶሻሊስት ግንባታ የሚያደርገውን ትግል በአስተማማኝ ሁኔታ ዋስትና በመስጠት የኒውክሌር ጦርነትን መከላከል ያስፈልጋል" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የሰሜን ኮሪያ የባሊስቲክ ሚሳኤሎች በዋሽንግተን፣ ሴኡል እና ቶኪያ የተወገዙ ከመሆናቸው በተጨማሪ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የተከለከሉ መሆናቸው ይታወቃል፡
“ሁዋሶንግ-17” የሚል ሲያሜ የተሰጠው ሚሳይል አሜሪከን መምታት የሚችል አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤል መሆኑ ይነገራል፡፡
ሚሳይሉ 1,000 ኪሜ (621 ማይል) ርቀት የመምዘግዘግ አቅም እንዳለውም ይነገራል፡፡