ሰሜን ኮሪያ አሜሪካና ደቡብ ኮሪያን ለማስጠንቀቅ የተኮሰችው ህዋሰኦንግ-17 ሚሳዔል እውነታዎች
ህዋሰኦንግ-17 አህጉር አቋራጭ ሚሳዔል “አውሬው” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን አሜሪካን የመምታት አቅም አለው
ከሰሜን ኮሪያ ሚሳዔሎች መካከል ህዋሰኦንግ-17 (አውሬው) ሚሳዔልን ምን የተለየ ያደርገዋል…?
ሰሜን ኮሪያ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ላይ ያሉትን አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያን ለማስጠንቀቅ የሁዋሶንግ-17 አህጉር አቋራጭ ሚሳይል (አይሲቢኤም) ማስቀንጨፏን አስታውቃለች።
ሀገሪቱ በትናንትነው እለት ከፒዮንግያንግ አውሮፕላን ማረፊያ ያስወነጨፈቸው ሚሳይል የጋራ ልምምድ በማካሄድ ላይ ላሉት ዋሽንግተን እና ሴኡል ጠንካራ ምላሽ ለመስጠት ነው ተብሏል።
ሰሜን ኮሪያ ለሙከራ ካስወነጨፈቻቸው ከሃይፐርሶኒክ እና አህጉር አቋራጭ (አይ.ሲ.ቢ.ኤም) ሚሳዔሎች መካከል “ህዋሰኦንግ-17 (አውሬው)” የሚል መጠሪያ የተሰጠው እንደሚገኝበትም ተነግሯል።
ህዋሰኦንግ-17 ሚሳዔል ምንድነው…?
ሰሜን ኮሪያ “ህዋሰኦንግ-17” ሚሳዔልን በፈረንጆቹ 2020 ባለካሄደችው ወታደራዊ ትርዒት ላይ በባለ 22 ጎማ ከባድ ተሸከርካሪ ላይ ጭና ለእይታ ማቅረቧ ይታወሳል።
የዘርፉ ባለሙያዎች “ህዋሰኦንግ-17” ሚሳዔልን “ግዙፉ” ወይም “አውሬው” ሲሉ የሚጠሩት ሲሆን፤ ሰሜን ኮሪያ ከዚህ ቀደም የነበራት “ህዋሰኦንግ-15” ላይ ቴክኒካዊ ማሻሻያዎች አድጋበት ነው ያቀረበችው ይላሉ።
ሚሳዔሉ አህጉር አቋራጭ (አይ.ሲ.ቢ.ኤም) ሚሳዔል አይነት ነው የተባለ ሲሆን፤ ሰሜን ኮሪያ ባሳለፍነው የካቲት እና አሁን ባለንበት መጋት ወር ላይ ለሙከራ ካስወነጨፈቻቸው መካከል እንደሚገኝ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ አስታውቀዋል።
የኒኩሌር አረርን ጨምሮ የተለያዩ የጦር መሳሪየ አረሮች ተሸካሚ የሆነው “ህዋሰኦንግ-17” ለመመከት አስቸጋሪ ነው የተባለለት ሲሆን፤ “ህዋሰኦንግ-17” የመሳሪውን አቅም በቅርቡ ይፋ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል።
እንደ ባለሙያዎቹ ገለጻ ፒዮንግያንግ የሰሜን ኮሪያ መስራች እንደሆኑ የሚነገርላቸው የኪም ኢል ሱንግ ልደት ቀን ማለትም የፊታችን ሚያዚያ 7 “ህዋሰኦንግ-17” ሚሳዔልን ልታስወንጭፍ ትችላለች።
አሜሪካን የመምት አቅም አለው የተባለለት ሃውሶንግ-17 ሚሳዔል ከ15 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የመጓዝ አቅም እንዳለው ተነግሯል።