የ83 ዓመቱ ጌንጎብ የፓን አፍሪካ ጽንሰ ሀሳብ አቀንቃኝ ነበሩ
የናሚቢያ ፕሬዝዳንት ሀጌ ጌንጎብ ህይወታቸው አለፈ፡፡
ጥቁሮችን ዝቅ የሚያደርጉ አስተያየቶችን በመቃወም የሚታወቁት የናምቢያ ፕሬዝዳንት ሀጌ ጌንጎብ ህይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ፕሬዝዳንቱ ከሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ወይም ፕሮስቴት ካንሰር ተጠቅተው ላለፉት ዓመታት ህክምና ሲከታተሉ ነበር፡፡
ከሰሞኑ ለዚሁ ህክምናቸው ወደ አሜሪካ ተጉዘው ህክምና አድርገው ተመልሰው ነበር የተባለ ሲሆን ዳግም ህመማቸው ተባብሶ ሀላፊነታቸውን ለምክትሎቻቸው አሳልፈው ሰጥተውም ነበር፡፡
የ83 ዓመቱ የናሚቢያ ዋነኛ የፖለቲካ ሰው ዛሬ ሌሊት ላይ ህይወታቸው አልፏል የተባለ ሲሆን ሀገሪቱ በሀዘን ላይ እንደምትገኝ ተገልጿል፡፡
አሁን ላይ ደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር ናሚቢያ በምክትል ፕሬዝዳንቱ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመመራት ላይ ነችም ተብሏል፡፡
ነዳጅ በርካሽ የሚሸጥባቸው የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
ሟቹ ፕሬዝዳንት በፈረንጆቹ 2014 ላይ ከፕሮስቴት ካንሰር ህመም ሙሉ ለሙሉ ማገገማቸውን ተናግረው የነበረ ቢሆንም ህመማቸው ዳግም አገርሽቶ ለሞት ዳርጓቸዋል፡፡
ናሚቢያ በያዝነው የፈረንጆቹ 2024 ዓመት ፕሬስዳንታዊ እና ህግ አውጪ ምክር ቤት ምርጫ ከሚያደርጉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን እስከ ምርጫ ድረስም በምክት ፕሬዝዳንት እየተመራች እንደምትቆይ ይጠበቃል፡፡
የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ድግሪያቸውን ዓለም አቀፍ ግንኙት ያጠኑት ሟቹ የናሚቢያ ፕሬዝዳንት ሀገራቸውን በጠቅላይ ሚኒስትርነት እና ፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል፡፡