ሞሮኮ እና ማሊ ወደ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ማለፋቸውን ያረጋገጡ የመጨረሻዎቹ ሀገራት ሆነዋል
የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታን አዘጋጅተው ዋንጫውን ያነሱ ሀገራት
የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በአህጉሪቱ ትልቅ ስፖርታዊ ውድድር ነው።
የዋንጫ ውድድሩ አዘጋጅ ሆኖ ዋንጫውን ማንሳት ደግሞ ለሀገራት ታሪካዊ የሚባል የእግር ኳስ ስኬት ነው።
በ46 አመታት ውስጥ በተካሄዱ 33 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች አስተናጋጅ ሀገራት 11 ጊዜ ዋንጫ ያነሱ ሲሆን ይህም 33 በመቶ ይሸፍናል።
በኮትዲቮር አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በርካታ ያልተጠበቁ ክስተቶችን እያስተናገደ ይገኛል።
ባሳየችው የጨዋታ አጀማመር ከምድቧ አታልፍም የተባለችው አስተናጋጇ ኮትዲቮር በአስደናቂ ሁኔታ የውድድሩን የ2021 አሸናፊ ሴኔጋልን አሸንፋ ወደ ሩብ ፍጻሜው ተቀላቅላለች።
የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች በትናንትናው እለት ሲጠናቀቁ ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉ ስምንት ሀገራትም ታውቀዋል።
ናይጀሪያ፣አንጎላ፣ ዲአር ኮኔጎ፣ ጊኒ፣ኬፕቨርዴ፣ ኮትዲቮር፣ማሊና እና ደቡብ አፍሪካ ወደ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታው አልፈዋል።
ሞሮኮ እና ማሊ ወደ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ማለፋቸውን ያረጋገጡ የመጨረሻዎቹ ሀገራት ሆነዋል።