ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ጠ/ሚኒስትር ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ እንዲያወጣ ጠየቀች
ደቡብ አፍሪካ ሀገራት ለእስራኤል ጦር የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያቆሙ አሳሰበች
የዓለም ፍርድ ቤት የእስራኤል ድርጊት የዘር ማጥፋት ሊሆን እንደሚችል ግልጽ ማድረጉን ደቡብ አፍሪካ ገለጸች
እስራኤል በጋዛ እየወሰደች ያለውን እርምጃ በቀዳሚነት ከተቃወሙ ሀገራት አንዷ የሆነችው ደቡብ አፍሪካ የዓለም የወንጀል ፍርድ ቤት በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእሰር ማዘዣ እንዲያወጣ ጠየቀች።
ደቡብ አፍሪካ ከዚህ ቀደም “እስራኤል በጋዛ በሚኖሩ ፍሊስጤማውያን ላይ የዘር ፍጅት እየፈጸመች ነው” በማት ሀገሪቱንም በዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት መክሰሷ ይታወሳል።
በሀገራት መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን የሚያስተናግደው ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ከሃማስ ታጣቂዎች ጋር ጦርነት በምታደርግበት ወቅት የዘር ማጥፋት ድርጊቶችን ለመከላከል እርምጃ እንድትወስድ ብይን መስጠቱም ይታወሳል።
አሁን ደግሞ ደቡብ አፍሪካ ጉዳዩን ወደ ዓለም የወንጀል ፍርድ ቤት ይዛ ያቀናች ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱ በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታንያሁ ላይ የእሰር ማዘዣ እንዲያወጣ መጠየቋን ሮይተርስ ዘግቧል።
የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ ጋር በፍሊስጤም ስላለው ጉዳይ በጋራ መነጋገራውን አስታውቀዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ፤ “ለአቃቤ ህጉ ፍርድ ቤቱ በሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ ለምን ለእስር ማዘዣ እንዳወጣ እና በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ ማውጣት ለምን እንደተሳነው ጠይቄዋለሁ” ብለዋል።
“አቃቤ ህጉ ቀጥተኛ መልስ አልሰጠኝም፤ ነገር ግን ከሁኔታዎች እንደተረዳሁት በጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ ለማውጣት ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ነው” ሲሉም ገልጸዋል።
በተያያዘ ዜና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት ለእስራኤል ጦር የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያቆሙ አሳስባለች።
የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር በጉዳዩ ላይ በሰጡተ አስተያየት የአለም ፍርድ ቤት እስራኤል በጋዛ እየፈጸመች ያለው ድርጊት የዘር ማጥፋት ሊሆን እንደሚችል አረጋግጧል ብለዋል።
ይህንን ተከትሎም ሁሉም ሀገራት ለእስራኤል ጦር የገንዘብ ድጋ ማድረግ እና ሁኔታዎችን ማመቻትን የማቆም ግዴታ አላባቸው ሲሉ ገልጸለዋል።
ደቡብ አፍሪካ የፍልስጤማውያንን ችግር በጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ላይ ሲደርስ ከነበረው ከአፓርታይድ በማነፃፀር በፍልስጤም ጉዳይ ጠበቃ ሆና ኖራለች።
እስራኤል በበኩሏ በደቡብ አፍሪክ የሚቀርብባትን የዘር ማጥፋት ወንጀላ እንደማትቀበል በመግለጽ፤ የፍሊስጤማውያንን ጉዳይ ከአፓርታይድ ዘመን ጋር ያለውን ንፅፅር ውድቅ አድርጋለች።