በፈረንጆቹ 2019 ሱዳን በጸረ-ሽብር ዘመቻ ተባባሪ መሆኗን አሜሪካ አስታወቀች
ከቀድሞው የሱዳን ፕሬዘዳንት አልበሽር ስልጣን መወገድ በኋላ ሻክሮ የነበረው የአሜሪካና ሱዳን ግንኙነት እየተሻሻለ ነው
አሜሪካ ሱዳንን በፈረንጆቹ 1993 ሽብርን ከሚደግፉት “ከሀማስና ከሂዝቦላህ “ጋር ፈርጃት እንደነበር ሪፖርቱ አካቷል
አሜሪካ ሱዳንን በፈረንጆቹ 1993 ሽብርን ከሚደግፉት “ከሀማስና ከሂዝቦላህ “ጋር ፈርጃት እንደነበር ሪፖርቱ አካቷል
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው የፈረንጆቹ “2019 የሀገራት ሽብርተኝነትን የተመለከተ ሪፖርት” ሱዳን በጸረ-ሽብር ዘመቻ ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር ለመተባበር እርምጃዎችን መውሰዷን አስታውቋል፡፡
ሱዳን ምንምእንኳን በፈረንጆቹ 2019 ሀገሪቱን ለሶስት አስርት አመታት ለሚጠጋ ጊዜ የመሩት የቀድሞው ፕሬዘዳንት ኦማር አልበሽር በህዝባዊ አመጽ ከስልጣን መወገድን ተከትሎ አለመርጋጋት ውስጥ ብትቆም፣ የሱዳን መንግስት ከቀጠናዊ የጸረ-ሽብር አጋሮች ጋር እየሰራች ነው ብሏል፡፡ ሪፖርቱ ሱዳን፣ የሱዳንና የአሜሪካን ጥቅም በሚጻረሩ ዘመቻዎች ላይ እየተሳተፈች መሆኑን ገልጿል፡፡
የአልበሽርን ከስልጣን መወገድ ተከትሎ፣ ሱዳንን እያስተዳደረ ያለው የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር መንግስት ከአሜሪካ መንግስት ጋር የነበረው አስርት አመታት ያስቆጠረውን አለመግባባት ለፍታት አምባሳደር እስከመሾም የደረሰ ሲሆን አሜሪካም በበኩላ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ችግር እንዲፈታ ፋላጎቷን አሳይታለች፡፡
ነገርግን ሪፖርቱ ትልቅ የሚባል የሽብር ጥቃት ባይኖርም የኤይኤስአይኤስ አስተባባሪዎች አሁን በሀገሪቱ አሉ ብሏል፡፡ እንደ ሪፖርቱ ከሆኑ በሱዳን አሁን የተሸሙት የሀይማኖትና ኢንዶውመንት ሚኒስትር በግልጽ የሚታወቅ የአይኤስአይኤስ ቡድን አካል የለም ያሉ ሲሆን ነገርግን ቡድኑን የሚደግፉ አክራሪዎች መኖራቸውን አልካዱም፡፡
ሱዳን በፈረንጆቹ 1993 ሽብርን ከሚደግፉት አቡናዳል፣ከፍልስጤም እስላማዊ ጅሀድ፣ ከሀማስና ከሂዝቦላህ ጋር በአሜሪካ ተፈርጃ ነበር፡፡