ከቁጥጥር ውጭ የሆነው የአሜሪከው ናሳ ሳተላይት ምድር ላይ ሊወድቅ መሆኑ ስጋት ፈጥሯል
11 ሺህ ኪሎ ግራም የሚመዝነው ሳተላይቱ ነገ እሁድ ወይም ሰኞ ጠዋት ምድር ላይ ሊወድቅ ይችላል ተብሏል
ሳተላይቱ በአፍሪካ፣ ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ፣ መካከለኛ ምስራቅ ወይም በኢሲያ ሀገራት ሊወድቅ ይችላል
ለ38 ዓመታት ያገለገለ እና ከአገልግሎት ውጪ የሆነ የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ማዕከል ናሳ ንብረተ የሆነ ሳተላይት ምድር ላይ ሊወድቅ እንደሆነ ተነግሯል።
ናሳ ባሳለፍነው ሳምንት አርብ እንዳስታወቀው ከሆነ፤ ሳተላይቱ በየትኛውም የምድር ክፍል ላይ የመውደቅ እድሉ ከፍተኛ ነው፤ ነገር ግን ጉዳት የማድረስ መጠኑ ዝቅተኛ ነው ብሏል።
- ከቁጥጥር ውጭ የሆነው የቻይና ሮኬት አካል ወደ ምድር እየተምዘገዘገ መሆኑ ስጋት ፈጥሯል
- ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ የነበረው የቻይናው ሮኬት ስብርባሪ ህንድ ወቅያኖስ ላይ አረፈ
እንደ ናሳ ገለጻ ከሆነ 11 ሺህ 850 ኪሎ ግራም ከሚመዝነው የሳተላይቱ አካል ውስጥ 2 ሺህ 450 ኪሎ ግራም ያክሉ በአየር ላይ እያለ የሚቃጠል ነው ብሏል።
ነገር ግን 9 ሺህ 400 ኪሎ ግራም የሚመዝን የሳተላይቱ ክፍል መሬት ላይ ሊደርስ እንደሚችል ስጋን አስታውቋል።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ከሆነ የሳተላይቱ ስብርባሪ እከ ነገ ምሽት ለው ጊዜ መሬት ላይ ሊወድቅ ይችላል።
መቀመጫውን ካሊፎርኒያ ያደረገው ኤሮስፔስ ኮርብፕ የተባለ ኩባያ በበኩሉ፤ የሳተላይቱ ስብርባሪ ሰኞ ጠዋት መሬት ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል።
አሮጌው የናሳ ሳተላይት ስብርባሪ በአፍሪካ፣ ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ፣ መካከለኛ ምስራቅ ወይም በኢሲያ ከሚገኙ ሀገራት ውስጥ በአንዱ ላይ ሊወድቅ እንደሚችልም ነው የተሰጋው።
ባሳለፍነው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ ከቁጥጥር ውጭ የሆነችው የቻይና ‘Long March-5B’ ሮኬት አካል በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ምድር እየተምዘገዘገች መሆኑ በረካቶች ዘንድ ስጋትን መፍጠሯ ይታወሳል።
ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ የነበረው የቻይና ሮኬት ስብርባሪ በትናንትናው እለት በህንድ ውቅያኖስ ላይ መውደቁም አይዘነጋም።