ፕሮጀክቱ 10 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ሲሆን በዓለም እስካሁን ከተሰሩት የህዋ መመልከቻዎች ግዙፉ ነው ተብሏል
የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ማእከል ናሳ በዌብ ስፔስ ቴሌስከፕ አማካኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ባለቀለም የሆነ ምስል ይፋ አድርጓል፡፡
ናሳ እንዳስታወቀው የተገጠመላትን መሳሪያ በስድስር ወራት ጊዜ ውስጥ የዘረጋችው ጄምስ ዌብ ስፔስ ቴሌስኮፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለሙሉ ቀለም ምስል ማንሳቷን ገልጿል፤ይህንም ለእይታ አቅርቧል፡፡
በዌብ ካሜራ የተነሳው ይህ ምስል የዌብ የመጀመሪያ ዲፕ ፊልድ የተሰኘ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ጋላክሲዎችን በዝርዝር አሳይቷል፡፡ ምስሉ በተለያየ ርቀት ላይ ያሉ የጋላክሲ ጥርቅሞችን ያሳያል፡፡
የዌብ 6 ነጥብ 5 ሜትር የወርቅ ሽፋን ያለው የመጀመሪያ ደረጃ መስታወት 18 ነጠላ ባለ ስድስት ጎን ክፍሎችን ያቀፈ ሲሆን በቴኒስ ሜዳ በሚያክል ባለ አምስት ሽፋን የፀሐይ መከላከያ የተጠበቀ ነው።
ፕሮጀክቱ 10 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ሲሆን በዓለም እስካሁን ከተሰሩት የህዋ መመልከቻዎች ግዙፉ መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡ የዌብ ቴሌስኮፕ ግዙፍ በሆነው የኤሮስፔስ ኩባንያ በኖርዝሮፕ ግሩማን ኮርፖሬሽን ተገንብቷል።
በጉጉት የሚጠበቀው የመጀመርያው ምስል ይፋ የሆነው የዌብ ቴሌስኮፕን የተለያዩ አካላትን በርቀት የመክፈት፣ መስተዋቶቹን እና የመለኪያ መሳሪያዎችን የማስተካከል የስድስት ወራት ሂደትን ተከትሎ ነው።
ናሳ ዌብ ቴሌስኮን ከካናዳና እና አውሮፓ የጠፈር ባለሙያዎች ጋር ነበር ከፍሬንች ጉያና በረንጆቹ 2021 ወደ ህዋ ያስወነጨፋት፡፡