ናሳ ከአስቴሮይዶች ጋር ተጋጭተው አቅጣጫቸውን ለማስቀየር የሚችሉ መንኮራኩሮችን አስወነጨፈ
መንኮራኩሮቹ ስፔስ ኤክስ ከተሰኘው ከቁጥር አንዱ የዓለማችን ቱጃር ኢሎን መስክ የጠፈር ኩባንያ ጋር በመተባበር ወደ ጠፈር የሚወነጨፉ ናቸው
ናሳ ይህን የሚያደርገው አስቴሮይዶቹ ወደ መሬት ተምዘግዝገው ህይወት ባለው ምድራዊ አካል ላይ ሊያደርሱ የሚችሉትን ጉዳት ለማስቀረት ነው
የአሜሪካ ብሔራዊ የኤሮኖቲክስ እና ህዋ አስተዳደር ተቋም (ናሳ) ተምዘግዝገው ወደ መሬት ሊወርዱና ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ አስቴሮይዶችን አቅጣጫ ለማስቀየር የሚያስችል ሙከራ (DART Mission) ሊያደርግ እንደሆነ አስታወቀ፡፡
ናሳ ለሙከራው የሚሆኑ መንኮራኩሮችን ወደ ጠፈር እንደሆነ አስታውቋል፡፡
ከግብጽ ፒራሚድ እና ከዋሽንግተን ሃውልት የሚገዝፉ አስቴሮይዶች በቀጣዮቹ ተከታታይ ቀናት ምድርን ያልፋሉ ተባለ
ሙከራው መንኮራኩሮቹ ወደ ምድር ከሚምዘገዘጉት አስቴሮይዶች ጋር ሆን ተብሎ እንዲጋጩ በማድረግ ነው የሚፈጸመው፡፡
ለዚህ የሚሆኑትን መንኮራኩሮች ስፔስ ኤክስ ከተሰኘው የቁጥር አንዱ የዓለማችን ቱጃር ኢሎን መስክ የጠፈር ኩባንያ ጋር በመተባበር ማዘጋጀቱንም ናሳ አስታውቋል፡፡
ሙከራው ዲሞርፎስ እና ዲዲሞስ የተሰኙ እና ለመሬት የቀረቡ ናቸው የተባለላቸውን አስቴሮይዶች በማጋየት ህይወት ባለው ምድራዊ አካል ላይ ጉዳት ሊያደርሱ በማይችሉበት ሁኔታ አቅጣጫቸውን ማስቀየር ነው፡፡
ናሳ በእርግጥ የደቀኑት ይህ ነው የሚባል አሁናዊ አደጋ የለም ያለላቸው ዲሞርፎስ እና ዲዲሞስ ጸሃይን በመዞር ላይ ናቸው፡፡
የአፖሎ 11 አብራሪ የነበረው ጠፈርተኛው ማይክል ኮሊንስ በ90 ዓመቱ አረፈ
ሁለት የአሜሪካን የነጻነት ሃውልት ያህል የሚገዝፈው ዲሞርፎስ 160 ሜትር (525 ጫማ) ያህል ዲያሜትር (ስፋት) አለው፡፡ ዲዲሞስ ደግሞ 2 ሺ 500 ሜትር ያህል ይሰፋል፡፡
ሙከራው እነዚህ አስቴሮይዶች ለመሬት በሚቀርቡበትና 11 ሚሊዮን ኬሎ ሜትሮችን ያህል በሚርቁበት በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ዓመት መገባደጃ አካባ የሚደረግ ነው፡፡
ይህን ለማድረግ የምትችለው የ ስፔስ ኤክስ መንኮራኩር ዛሬ ካሊፎርኒያ ከሚገኝ ማዕከል ወደ ጠፈር ተወንጭፋለች፡፡
እስካሁን ለምድር በቀረበ ርቀት ላይ እንደሚገኙ የታወቁ 10 ሺ አስቴሮይዶች አሉ፡፡ ነገር ግን በሚቀጥሉት 100 ዓመታት ውስጥ አንዳቸውም ምድርን የመምታት አጋጣሚ የላቸውም።
ወደ መሬት በመምዘግዘግ ላይ ካሉት አስቴሮይዶች መካከል ነው የተባለለትና የመጀመሪያው አስቴሮይድ ባሳለፍነው በፈረንጆቹ ጥቅምት 15 መሬትን እንደሚያልፍ ይጠበቃል ተብሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡