በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ዋዜማ ይመጥቃል የተባለለት ቴሌስኮፑ የከዋክብትን አፈጣጠር ስርዓት ለማጥናት ወሳኝ ነው ተብሏል
የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ተቋም (ናሳ) በመጪው ሳምንት አርብ “ጄምስ ዌብ” (JWST) የተሰኘ ግዙፍ የጠፈር ምርምር ቴሌስኮፕን እንደሚያመጥቅ አስታወቀ፡፡
እ.ኤ.አ ታህሳስ 24 ይወነጨፋል የተባለለት ግዙፉ “ጄምስ ዌብ” ቴሌስኮፕ በናሳ እንዲሁም በአውሮፓ እና በካናዳ የጠፈር ምርምር ማዕከላት ትብብር የተገነባ ነው፡፡
“ጄምስ ዌብ” በጥቅሉ 10 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ገንዘብ ወጥቶበታል፡፡
ወደ ጠፈር ለመጓዝ 60 ዓመታትን የጠበቁት አዛውንት ሊጓዙ ነው
‘አርያን 5’ በተባለ ሮኬት ተጭኖ ነው ከፍሬንች ጉያና ወደ ጠፈር የሚጓዘው፡፡ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ያህል ኪሎ ሜትሮች ይርቃልም ብለዋል የጠፈር ሳይንቲስቶቹ፡፡
ቴሌስኮፑ አጠቃላይ የስርዓተ ከዋክብትንና የጠፈርን አፈጣጠር ለማጥናት ያስችላል ተብሏል፡፡
የአፖሎ 11 አብራሪ የነበረው ጠፈርተኛው ማይክል ኮሊንስ በ90 ዓመቱ አረፈ
እጅግ ርቀው የሚገኙ እና የሰው ልጅ ደርሶ ለማየት የማይችላቸውን የጠፈር አካላት ለማየትና ለማጥናት እንደሚያስችለውም ነው ናሳ ያስታወቀው፡፡
ከዋክብቶች እና አጠቃላይ ስርዓተ ከዋክብት ከ14 ቢሊዮን ዓመታት በፊት እንዴት እንደተፈጠሩ ለማወቅ ወሳኝ ነውም ነው ተቋሙ የሚለው፡፡
ለጥቂት ደቂቃዎች ወደ ጠፈር ለመጓዝ የአንድ ወንበር የጨረታ ዋጋ ከ2 ነጥበ 4 ሚሊዮን ዶላር አለፈ
“ጄምስ ዌብ” ዛሬ ቅዳሜ ነበር ወደ ጠፈር ይጓዛል የተባለለት፡፡ ሆኖም በገጠሙት የቴክኒክ ችግሮች ምክንያት አንድ ሳምንትን መዘግየት ግድ ብሎታል፡፡
ሳምንት አርብ እንዲወነጭፍ አስፈላጊ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውንም ነው ናሳ ያስታወቀው፡፡
ናሳ በ1990ዎቹ መባቻ ሃብል የተሰኘ የምርምር ቴሌስኮፕ (HST) ወደ ጠፈር መላኩን የተቋሙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡