ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ አሳሰበ
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ አሳሰበ
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ አሳሰበ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከውጭ ምንዛሪ ግብይት ጋር በተያያዘ ስለሚፈጸሙ ክፍያዎች የማሻሻያ ፖሊሲ ይፋ አድርጓል::
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
በዚህም ባንኮች በየእለቱ በሚያወጡት የውጭ ምንዛሬ የዋጋ ተመን ላይ በመግዣ እና በመሸጫው መካከል ከ10 በላይ ልዩነት ሲታይበት ቆይቷል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ዛሬ ጠዋት ባወጣው መግለጫው፤ አዲሱ የምንዛሬ ተመን አሰራር ይፋ መሆኑን ተከትሎ በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ ያሉ ሂደቶችን ሲከታተል መቆየቱን አስታውቋል።
ብሔራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት በአለም አቀፍ አሰራር መሰረት መሆን እንዳለበት አመልክቷል።
በመሆኑም የውጭ ምንዛሬ መግዣና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት ከሁለት በመቶ በላይ መሆን እንደሌለበት ነው ባንኩ በመግለጫው ያሳሰበው።
ብሔራዊ ባንኩ ይህንን በተመለከተ ለንግድ ባንኮች በደብዳቤ ማሳወቁን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባክ በመግለጫው አክሎም፤ አሁንም ቢሆንም ባንኮች የምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን በራሳቸውና ከደንበኞቻቸው ጋር ባላቸው ስምምነት ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቁሟል።
ንግድ ባንኮች የምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን በተናጠል በየቀኑ ማሳወቃቸውን መቀጠል እንዳለባቸውም ነው ብሄራዊ ባንክ ያስታወቀው።
ባንኮች ከውጭ ምንዛሬ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የሚጠይቋቸውን ኮሚሽኖች ከምንዛሬ መሸጫ ጋር ሳይሆን በተናጠል ለደንበኞቻቸው እንዲያሳውቁሞ አዝዟል።
የብሄራዊ ባንክን ማሳሰቢያ ተከትሎ ባንኮች በዛሬው እለት እያወጡት ባለው የዋጋ ተመን ላይ የመሸጫ ዋጋ ላይ ከ10 ብር በላይ ቅናሽ እደረጉ ነው።
ለአብነትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዛሬው እለታዊ የዋጋ ዝርዝር መሸጫ ዋጋውን ከ123 ወደ 115 ዝቅ አድርጓል።