የኔቶ መሪዎች በስፔን ማድሪድ ባካሄዱት ስብሰባ ሩሲያን የደህንነት ስጋት አድርገው ፈርጀዋል
ሩሲያ በሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በስጋትነት መፈረጇ ትክክል አይደለም ስትል ተቃወመች።
ኔቶ ሩሲያን ጠላት አድርጎ የፈረጀው በሁሉም ግንባሮች ለመውጋት እንደሆነም ሞስኮ አስታውቃለች።
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፤ የኔቶ ፍረጃ አግባብ አለመሆኑን ገልጾ ይህ ሞስኮን በሁሉም መልኩ የማጥቃት ስልት ነው ብሏል።
ኔቶ ሩሲያ ቀጥተኛ ስጋቴ ናት ማለቱ ከሩሲያ ጋር ለመጋጨት ያለመ ነውም ብሏል።
ይህ የኔቶ ፍረጃ ሩሲያን በሁሉም ግንባሮች፤ በሁሉም መንገድ ለማጥቃት ያለመ እንደሆነም ነው የሰርጌ ላቭሮቭ መስሪያ ቤት ያስታወቀው።
ኔቶ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ለተነሳው ጦርነት ወነኛ ምክንያት ቢሆንም ከዩክሬን ጎን ሆኖ መዋጋትን አለመምረጡን ገልጾ ነበር።
ዋና ጸሐፊው ጀንስ ስቶልተንበርግ ተቋማቸው ከዩክሬን ግን ሆኖ ሩሲያን ቢወጋ 3ኛው የዓለም ጦርነት ሊነሳ ይችላል ማለታቸው ይታወሳል።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው ኔቶን "ደካማና ረብ የለሽ" ማለታቸው ይታወሳል።