ጠ/ሚኒስትር ኔታንያሁ ቤታቸው ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በሰጡት የመጀመሪያ አስተያየት ምን አሉ?
ከሊባኖስ የተነሳ ድሮን የጠ/ሚኒስትር ኔታንያሁን መኖሪያ ቤት መምታቱን የእስራኤል ጦር አስታውቋል
በድሮን ጥቃት የተፈጸመበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ መኖሪያ ሰሜን ቴል-አቪቭ ቄሳሪያ አካባቢ የሚገኝ ነው
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሆ በመኖሪያ ቤታቸው ላይ የደሮን ጥቃት ከተፈጸመ ከሰዓታት በኋላ አስተያየት ሰጥተዋል።
ዛሬ ጠዋት ላይ መነሻው ከሊባኖስ የሆነ ድሮን በቄሳሪያ የሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስተር ኔታንያሆ መኖሪያ ቤት ላይ በቀጥታ ጥቃት መፈጸሙን የእስራኤልጦር አረጋግጧል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጥቃቱ ከተፈጸመ ከሰዓታት በኋላ በማህበራዊ ትስስር ገጽ በቪዲዮ የተቀረጸ መስል መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ “ምንም የሚያስቆመኝ ነገር የለም” ብለዋል።
እስራኤል ጦርነቱን እንደምታሸንፍ ቃል የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ፤ ከጥቅምት 7 ጥቃት የጀርባ ያለውን ዋነኛው ሰው ነው ያሉትን የሃማስ መሪ ያያ ሲንዋርን ስም በመጥቀስ “አስወግደነዋል” ብለዋል።
“የኢራን ተላላኪ ከሆኑ አሸባሪዎች ጋር የምናደርገውን ውጊያ ቀጥለናል፤ ከማሸነፍ የሚያቆመን ነገር የለም ሲሉም” ተናረዋል።
የእስራኤል ጦር የድሮን ጥቃቱን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፤ መነሻው ከሊባኖስ የሆን ድሮን በቄሳሪያ የሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስተር ኔታንያሆ መኖሪያ ቤት ላይ በቀጥታ ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጧል።
ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታንያሁ እና ባለቤታቸው እንዲሁም ቤተሰቦቻው በቤቱ ውስጥ እንዳልነበሩ እና በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ነው የእስራኤል ጦር ያስታወቀው።
እስራኤል በሊባኖስ የትምታካሂደውን የአየር ድብደባ እና የእግረኛ ጦር ውጊያ የቀጠለች ሲሆን፤ ሄዝቦላህም ራሱን ለመከላከል በእስራኤል ጦር ላይ መጠነ ሰፊ እና የተሳኩ ጥቃቶችን እየፈጸመ ይገኛል።
ሄዝቦላህ ከእስራኤል የተከፈተበትን ጥቃት ለመመከት አዲስ እና ሚስጥራዊ ወታደራዊ እዝ መመሰረቱም ይታወሳል።
አዲሱ የሄዝቦላህ ወታደራዊ እዝ ሮኬቶች እና ሚሳዔሎች እንዲተኮሱ ትዝዛዝ የሚሰጥ እና የምድር ላይ ውጊየዎችን የሚመራ እንደሆነም ተነግሯል።
ሄዝቦላህ አሁንም ቢሆን በርካታ መሳሪያዎች በእጁ እንዳለ የሚነገር ሲሆን፤ ከታጠቃቸው መሳሪያዎች መካልም ከዚህ ቀደም ጥቅም ላይ ያላዋላቸው አደገኛ ሚሳዔሎች ይገኙበታል ነው የተባለው።