ሄዝቦላህ በእስራኤል ጠ/ሚኒስትር ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ የድሮን ጥቃት ፈጸመ
ከሊባኖስ የተነሳ ድሮን የጠ/ሚኒስትር ኔታንያሁን መኖሪያ ቤት መምታቱን የእስራኤል ጦር አስታውቋል
በድሮን ጥቃት የተፈጸመበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ መኖሪያ ሰሜን ቴል-አቪቭ ኬሳሪያ አካባቢ የሚገኝ ነው
የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ቡድን በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸመቱ ተሰምቷል።
የድሮን ጥቃቱ በሰሜን ቴል-አቪቭ ኬሳሪያ አካባቢ የሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ መፈጸሙ ነው የተነገረው።
የእስራኤል ጦር ጥቃቱን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፤ መነሻው ከሊባኖስ የሆን ድሮን በኬሳሪያ የሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስተር ኔታንያሆ መኖሪያ ቤት ላይ በቀጥታ ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጧል።
ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታንያሁ እና ባለቤታቸው እንዲሁም ቤተሰቦቻው በቤቱ ውስጥ እንዳልነበሩ እና በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ነው የእስራኤል ጦር ያስታወቀው።
የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ መኖሪያ የሚገኝበት ኬሳሪያ አካባቢ የሄዝቦላህ የጥቃት ኢላማ ሲሆን ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም መስከረም 24 ላይ ጥቃት ተፈጸሞበት ነበር።
እስራኤል በሊባኖስ የትምታካሂደውን የአየር ድብደባ እና የእግረኛ ጦር ውጊያ የቀጠለች ሲሆን፤ ሄዝቦላህም ራሱን ለመከላከል በእስራኤል ጦር ላይ መጠነ ሰፊ እና የተሳኩ ጥቃቶችን እየፈጸመ ይገኛል።
ሄዝቦላህ ከእስራኤል የተከፈተበትን ጥቃት ለመመከት አዲስ እና ሚስጥራዊ ወታደራዊ እዝ መመሰረቱም ይታወሳል።
አዲሱ የሄዝቦላህ ወታደራዊ እዝ ሮኬቶች እና ሚሳዔሎች እንዲተኮሱ ትዝዛዝ የሚሰጥ እና የምድር ላይ ውጊየዎችን የሚመራ እንደሆነም ተነግሯል።
ሄዝቦላህ አሁንም ቢሆን በርካታ መሳሪያዎች በእጁ እንዳለ የሚነገር ሲሆን፤ ከታጠቃቸው መሳሪያዎች መካልም ከዚህ ቀደም ጥቅም ላይ ያላዋላቸው አደገኛ ሚሳዔሎች ይገኙበታል ነው የተባለው።