የኔዘርላንዷ ሃርለም ከተማ የስጋ ማስታወቂያዎችን በማገድ በዓለም የመጀመሪያዋ ከተማ ልትሆን ነው
እገዳው ሁሉንም ከእንስሳት እርባታ የሚገገኙ 'መጥፎ' የስጋ ማስታወቂያዎች ላይ ያነጣጠረ ነው ተብሏል
በኔዘርላንድ የስጋ ኢንዱስትሪ እና አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ርምጃው “ስጋ ተመጋቢዎችን ማጥላላት ነው” ሲሉ ተቃውመውታል
የኔዘርላንዷሃርለም ከተማ የስጋ ማስታወቂያዎችን በማገድ በዓለም የመጀመሪያዋ ከተማ ልትሆን ነው፡፡
ከተማዋ የስጋ ማስታወቂያዎችን የምትከለክለው በአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ሳቢያ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ለአምስተርዳም ቅርብ በሆነ ስፍራ ላይ የምትገኘውና የ160 ሺህ ሰዎች መኖሪያ እንደሆነች የሚነገርላት ሃርለም ከተማ ከ2024 ጀምሮ እንደ አውቶቡሶች፣ መጠለያዎች እና ስክሪኖች ባሉ የህዝብ ቦታዎች ላይ የስጋ ማስታወቂያዎችን እንደምትከለክል የከተማዋ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡
ርምጃው በህዳር ወር በከተማው ምክር ቤት የጸደቀ ቢሆንም አንድ የምክር ቤት አባል የማስታወቂያ ኤጀንሲዎች ወሳኔው በይፋ እንዲያውቁት መደረጉን እስገለጹበት እስካለፈው ሳምንት ድረስ ብዙም ሳይታወቅ ቆይቷል፡፡
የግሮኤንሊንክስ (ግሪን-ሌፍት) ፓርቲ የምክር ቤት አባል የሆኑት ዚጊ ክላዝዝ 'መጥፎ' የስጋ ማስታወቂያዎችን ለመከልከል የመጀመሪያዋ ከተማ ትሆናለች “ ማለታቸው ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
“የከተማውን የህዝብ ቦታ የዓለም ሙቀት መጨመርን የሚያፋጥኑ ምርቶችን በማከራየት ገንዘብ ማግኘት ከከተማው ፖለቲካ ጋር የሚጋጭ ነው” ሲሉም ተናግረዋል የምክር ቤት አባሏ ዚጊ ክላዝዝ፡፡
እገዳው ሁሉንም “ከእንስሳት እርባታ የሚገኝ እርካሽ ስጋ” ላይ ያነጣጠረ ነውም ብለዋል፡፡
ከተማዋ የኦርጋኒክ ስጋ ማስታወቂያዎችን ለመከልከል ስለመወሰኗ ግን የምክር ቤት አባሏ ዚጊ ክላዝዝ ያሉት ነገር የለም፡፡
እገዳው በኔዘርላንድ የስጋ ኢንደስትሪ እና አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተተችቷል፡፡
ተቺዎቹ፤ ርምጃው “እንደ ሳንሱርና ስጋ ተመጋቢዎችን የማጥላላት” ጉዳይ አድርገን ነው የምንቆጥረውም ብለዋል ፡፡
የቀኝ ክንፍ ፓርቲ የሃርለም ምክር ቤት አባል የሆኑት ጆይ ራዴሜከር በሰጡት መግለጫ “ለፖለቲካዊ ምክንያቶች ማስታወቂያዎችን ማገድ አምባገነናዊ ነው” ሲሉ ተቃውሞአቸው ገልጸዋል።