ኤርዶሃን፤ የኤጂያን የአየር ክልል ጥሳለች ባሏት ግሪክ ላይ "ከባድ ዋጋ ያስከፍልሻል" ሲሉ ዝተዋል
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ግሪክ በኤጂያን የአየር ክልል ላይ በሚንቀሳቀሱት የቱርክ አውሮፕላኖች ላይ የምትፈጥርው “የማስጨነቅ ድረጊት” የማታቆም ከሆነ አጻፋው ከባድ እንደሚሆን ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በጥቁር ባህር አከባቢ በተደረገ ሰልፍ ባደረጉት ንግግር “ሄይ ግሪክ፣ ታሪክን ተመልከቺ፤ከዚህ በላይ የምትሄጂ ከሆነ ብዙ ዋጋ ትከፍያለሽ” ሲሉም ዝተዋል፡፡
የፕሬዝዳንቱ ዛቻ ስጋት ውስጥ የከተታት አቴንስም ታዲያ እየደረሰብኝ ያለውን ዛቻ ስጋት ፈጥሮብኛል ዓለም ይወቅልኝ እያለች ነው፡፡
ግሪክ ዓለም የአንካራን ባህሪ እንዲያወግዝ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለኔቶ እና ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት መላኳንም ነው ሮይተርስ የዘገበው፡፡
ቱርክ በቅርብ ወራት ወዲህ አቴንስ ግጭት ቀስቃሽ ድርጊቶች እየፈጸመች እንደሆነና ይህም የተጀመረውን የሰላም ጥረት ሚያበላሽ መሆኑ ስትገልጽ መቆየቷ ይታወቃል፡፡
ሀገራት ከቱርክ የባህር ጠረፍ አቅራቢያ በሚገኙ የግሪክ ደሴቶች ዙሪያ በየቀኑ የአየር ሃይል ጥበቃዎችንና የመጥለፍ ተልእኮ እንቅስቀሰሴዎች የሚያደረጉ ሲሆን ለረዥም ጊዜ የቆዩ የባህርና የአየር ወሰን አለመግባባቶች እንዳሏቸው ይታወቃል።
አቴንስ፤ አንካራ በግሪክ ደሴቶች የአየር ክልል ላይ የምታደርገው በረራ ተንኳሽ ነው ስትል ትከሳለች፡፡
ቱርክ በበኩሏግሪክ ከአንደኛውና ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተፈራረሙትን የሰላም ስምምነቶች በመጣስ ወታደሮቿን በኤጂያን ባህር ደሴቶች ላይ እያሰፈረች ነው የሚል ክስ ስታቀርብ ትደመጣለች፡፡
ኤርዶሃን ሰሞኑን ባደረጉት ንዴት የተቀላቀለበት ንግግር ግሪክ ደሴቶቹን "ይዛለች" ብለዋል።
በ 1922 የቱርክ ኃይሎች በኤጂያን የባህር ዳርቻ ወደ ከተማዋ ከገቡ በኋላ የግሪክን ወረራ ማብቃቱን ያስታወሱት ኤርዶሃን “ግሪክን የምንነግራት አንድ ቃል ብቻ ነው፡- ኢዝሚርን (ቀደም ባሉ ጊዜያት ቱርኮች አሸነፊ ሆነው የተቆጣጠሩት ስፋራ) አትርሺ ” ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።
በደሴቶቹ ላይ ያደረግሺው ወረራ እኛን አያስተሳስረንም ያሉት ፕሬዝዳንቱ "ጊዜው ሲደርስ አስፈላጊውን ነገር እናደርጋለን። እንደምንለው፣ አንድ ሌሊት በድንገት ልንመጣ እንችላለን”በማለትም ነው ፕሬዝዳንቱ በጎረቤት ሶሪያን ኦፕሬሽን ለማድረግ ባሰቡ ወቅት ደጋግመው ሲጠቀሙባቸው የነበሩትን ቃላቶች በኤቴንስ ላይ የሰነዘሩት፡፡
የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ አቴንስ ወታደሮቿን ወደዚያ (ደሴቶቹ) መላክ ከቀጠለች አንላራ የግሪክን ሉዓለዊነት ልትፈታተን እንደምትችል ባሳለፍነው ወርሃ ሰኔ ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት ማስተላለፋቸው አይዘነጋም፡፡