የሆላንድ ተማሪዎች በጸሀይ ብርሃን የምትሰራ መኪና መስራታቸውን ገለጹ
አዲሷ ተሽከርካሪ የጸሀይ ብርሃን እስካለ ድረስ ያለ ነዳጅ እና ቻርጅ መስራት እንደምትችልም ተገልጿል
በአየንዶቨን ዩንቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ተማሪዎች የተሰራችው ይህች ተሽከርካሪ በቀን እስከ 630 ኪሎ ሜትር ትጓዛለች ተብሏል
የሆላንድ ተማሪዎች በጸሀይ ብርሃን የምትሰራ መኪና መስራታቸውን ገለጹ፡፡
በሆላንዱ አየንዶቨን ዩንቨርሲቲ ዩንቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ተማሪዎች በጸሀይ ሀይል የምትሰራ ተሽከርካሪ መስራታቸውን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ተማሪዎቹ የሰሩት ተሽከርካሪ በቀን እስከ 630 ኪሎ ሜትር ርቀት መጓዝ ይችላል የተባለ ሲሆን ተማሪዎቹ ወደ ሞሮኮ በመምጣት ሙከራ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
ተሽከርካሪዋ በሞሮኮ ጎዳናዎች ላይ የ1 ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀት ሙከራ አድርጋለች የተባለ ሲሆን የለምንም ችግር መንዳት ተችሏል ተብሏል፡፡
ባለሁለት መቀመጫ ያላት ይህች ተሽከርካሪ በጸሀይ ሀይል የሰራች የዓለማችን የመጀመሪያዋ ተሽከርካሪ ስትሆን በተሽከርካሪዋ ላይ በተገጠመላት የጸሀይ ሀይል መሳቢያ አማካኝነት እንደምትሰራ ተገልጿል፡፡
የአሜሪካው የቴክኖሎጂ ኩባንያ በራሪ ተሽከርካሪ መስራቱን ገለጸ
በቂ የጸሀይ ሀይል ባለባቸው አካባቢዎች ሁሉ ትስራለች የተባለችው ይህች ተሽከርካሪ የተወሰኑ ማስተካከያዎች ከተደረጉላት በኋላ ለገበያ ትቀርባለች ተብሏል፡፡
በዓለማችን የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት እየጨመረ መሄዱን ተከትሎ በነዳጅ ይሰሩ የነበሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ መቀየር የተቻለ ሲሆን የጸሀይ ሀይል ደግሞ በአማራጭነት መምጣቱ ጥሩ እድል እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
በርካታ የዓለማችን ሀገራት በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ቁጥር እየቀነሱ ሲሆን ከ2030 በኋላ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ በታዳሽ ሀይል ብቻ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ መጠቀም ለመግባት እቅድ ተይዟል፡፡