የወላይታ ዞን ምክር ቤት የዞኑ የክልልነት ጥያቄ ምላሽ ካልተሰጠው ጉዳዩን ወደ ፌዴሬሸን ም/ቤት እወስዳለሁ አለ
የደቡብ ክልል ምክር ቤት አንድ አመት ሊሞላው ጥቂት ቀናት ለቀረው የወላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ በአጭር ጊዜ ውሰጥ ምላሸ ካለሰጠ ጉዳዩን በአቤቱታነት ወደ ፌዴሬሸን ምክር ቤት እንዲወሰድ የቀረበለትን አጄንዳ የወላይታ ዞን ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ አፀደቀ::
የወላይታ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የሰራ ዘመን 1ኛ አሰቸኳይ ጉባኤውን ዛሬ ህዳር 30 ቀን 2012 ዓ.ም. እያካሄደ ይገኛል::
የምክር ቤቱ አባላት አሰቸኳይ ጉባኤ የተጠሩት የወላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ የደረሰበትን ደረጃ ለመገምገም እና ቀጣይ አቅጣጫ ለማሰቀመጥ ነወ ተብሏል::
የወላይታ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ የኢትዮጵያ ህገ - መንግሰት በሚፈቅደው መሰረት ለደቡብ ክልል ምክር ቤት የቀረበ ቢሆንም ምክር ቤቱ ግን ሀላፊነቱን ችላ በማለት ለሀገሪቱ ምርጫ ቦርድ አለመራልንም ያሉት የወላይታ ዞን ምክር ቤት አፌ ጉባኤ ወ/ሮ አበበች እራሾ ምክር ቤቱ አሰቸኳይ ጉባኤ የተጠራበት ዋነኛው ምክንያትም ይሄው መሆኑን ተናግረዋል::
የወላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ከቀበሌ እሰከ ዞን ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት ታህሳስ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. የዞኑ ምክር ቤት በክልል የመደራጀት ጥያቀውን አፅድቆ ውሳኔ አሳልፏል::
ጥያቄው ለደቡብ ክልል ምክር ከቀረበ አንድ አመት ሊሞላው 10 ቀናት የቀረው ሲሆን በቀሪዎቹ ቀናት ምክር ቤቱ አሰቸኳይ ምላሸ መሰጠት ካልቻለ ጉዳዩን ወደ ፌደሬሸን ምክር ቤት በመውሰድ አቤቱታ እንደሚያቀርብ ዞኑ አስታውቋል::
ጥያቄው ህጋዊ ሂደቱን ጠብቆ ምላሸ እንዲያገኝ ከክልሉ እና ከፌደራል የመንግሰት አካላት ጋር ተደጋጋሚ ምክክር ቢደረግም ውጤት አልባ ነበር ተብሏል::
በሂደቱ ዙሪያ ለምክር ቤቱ ሪፖርት ያቀረቡት የወላይታ ዞን ዋና አሰተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩንቤ የደቡብ ክልል ምክር ቤት የወላይታ ህዝብ ጥያቄን አክብሮ አላስተናገደም፤ በህገመንግሰቱ መሰረት ጥያቄውን ማየት ነበረበት ብለዋል::
በቅርቡ የወላይታ ህዝብን የወከለ ቡድን ከጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በ ቤተ መንግሰት ምክክር ማድረጉ የሚታወሰ ነው::
አል-ዐይን ሀዋሳ