ሞስኮ በጋዛ የሚደርሰውን ሰብዓዊ አደጋ ለመከላከል እርዳታ ማድረግ እንደምትፈልግ ተናገረች
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ከፍተኛ መሪ በእስራኤል እስር ቤት የሚገኙትን ፍልስጤማውያንን በሙሉ ለማስፈታት መላው በእጃቸው እንደሆነ ተናግረዋል።
መሪው ሀማስ ያገታቸውን እስራኤላውያን እንደ መደራደሪያ ሊጠቀምባቸው እንደሚችል አመላክተዋል።
ሀማስ በጋዛ ውስጥ ከ200 እስከ 250 የሚጠጉ የእስራኤል ምርኮኞች እንዳሉት የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
የእስራኤል ምርኮኞች የጋዛ ዞን ከፍተኛ መኮንኖችን ያካትታሉ ተብሏል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ረቡዕ ወደ እስራኤል አቅንተው ከፍተኛ ጉብኝት ያደርጋሉም ተብሎ ይጠበቃል።
በጋዛ ሰብዓዊ ቀውስ ያስከተለው የእስራኤልና ሀማስ ጦርነት፤ ከኢራን ጋር ሰፋ ያለ ያለ ፍጥጫ ፈጥሯል።
የቡድን ሰባት ፕሬዝዳንት ጃፓን በጋዛ ለሚኖሩ ንጹሀን ዜጎች 10 ሚሊየን ዶላር እርዳታ እንደምትሰጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ የጋዛን ሁኔታ አሳሳቢ በማለት የገለጹ ሲሆን፤ ሁኔታውን በትኩረት እየተከታተሉ እና ከኢራን አቻቸው ጋር ለመነጋገር የመጨረሻ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።
ዲፕሎማቶች ከበባ ላይ ላለው የጋዛ ሰርጥ የእርዳታ ጥሪያቸውን ዳግም አሰምተዋል።
የግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የፍልስጤምና የእስራኤል ግጭት የአከባቢውን ጸጥታ አደጋ ላይ እንዳይጥል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ባደረጉት የስልክ ልውውጥ አስምረውበታል ተብሏል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ለጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ ሞስኮ በጋዛ የሚደርሰውን ሰብዓዊ አደጋ ለመከላከል እርዳታ ማድረግ እንደምትፈልግ ተናግረዋል።