የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እስራኤልን ሊጎበኙ መሆኑ ተገለጸ
አሜሪካ ከጥቃቱ በኋላ የመጀመሪያውን ተግባራዊ ምላሽ የሰጠችው የጦር ጀቶቾን መሸከም የሚችሉ ግዙፍ የጦር መርከቦችን ወደ እስራኤል በማስጠጋት ነበር
የጋዛ ነዋሪዎች ውሃ፣ ምግብ እና መብራት እንዳያገኙ ያደረገችው እስራኤል በእግረኛ ወታደር ዘመቻ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ነች
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በመጭው ሮብዕ እስራኤልን ይጎበኛሉ።
ፕሬዝደንቱ ይህን ጉብኝት የሚያደርጉት እስራኤል በሀማስ ላይ እየወሰደችው ያለውን እርምጃ አጠናክራ በመቀጠችበት እና የሰብአዊ ቀውስ በተፈጠረበት ወቅት ነው።
የባይደን ጉብኝት ባልተጠበቀው የሀማስ ጥቃት 1300 ዜጎቿ ለተገደሉባት እና የአሜሪካ የመካከለኛው ምስራቅ አጋር ለሆነችው እስራኤል ድጋፍ ለማሳየት የታሰበ ነው ተብሏል።
እስራኤል የሀማስ ይዞታ የሆነችውን ጋዛን በመክበብ ያለማቋረጥ የአየር ድብደባ እያካሄደች ነው፣ በድብደባውም በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ሲገደሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ተፈናቅለዋል።
ባለፈው ማክሰኞ የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጋር ለሰአታት የቆየ ምከክር አድርገዋል።
ብሊንከን እስራኤል ከጥቃት ህዝቧን ለመከላከል ምን እንደሚያስፈልጋት ለመጠየቅ ባይደን እንደሚመጡ ተናግረው ነበር።
ባይደን ሀማስ በደቡባዊ እስራአል ድንበር ጥሶ በመግባት ያደረሰውን ጥቃት ባወገዙበት መግለጫቸው፣ አሜሪካ እስራኤል ራሷን ለመከላከል አስፈላጊውን ሀሉ ማሟላቷን እንደምታረጋግጥ መናገራቸው ይታወሳል።
አሜሪካ ከጥቃቱ በኋላ የመጀመሪያውን ተግባራዊ ምላሽ የሰጠችው የጦር ጀቶቾን መሸከም የሚችሉ ግዙፍ የጦር መርከቦችን ወደ እስራኤል በማስጠጋት ነበር።
የጋዛ ነዋሪዎች ውሃ፣ ምግብ እና መብራትን ጨምሮ ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዳያገኙ ያደረገችው እስራኤል በእግረኛ ወታደር ዘመቻ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ነች።