ኤችአይቪ እና ካላዛር በሽታን ለማከም የወጣው መመሪያ ውጤታማ መሆኑን ድርጅቱ ገለጸ
አዲሱ የህክምና መመሪያ በኢትዮጵያ 88 በመቶ እና በህንድ ደግሞ 96 በመቶ ውጤታማነት አሳይቷል ተብሏል
ድርጅቱ የክህምና መመሪያው በኢትዮጵያ እና በህንድ ውጤታ መሆኑ በጥናት ተረጋግጧል ብሏል
የዓለም ጤና ድርጅት የኤች አይ ቪ ኤድስ እና ካላዛር በሽታን ህክምና ለማዘመን የወጣው መመሪያ ውጤታማ በሆኑን በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል፡፡
ድርጅቱ በኢትዮጵያ እና በህንድ የተጠኑ ጥናቶች መመሪያው ውጤታማ መሆኑን ያሳያሉ ብሏል፡፡ ትኩረት የተነፈጉ በሽታዎች ላይ ትኩረት የሚያደርገው (ዲኤንዲ) ኢኒቲዬቲቭ፤የአለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሀኪሞች እና ሌሎች አካላት በትብብር ባጠኑት ጥናት መሰረት አዲሱ የህክምና መመሪያ ውጤታማ ነው፡፡
አዲሱ የህክምና መመሪያ በኢትዮጵያ 88 በመቶ እና በህንድ ደግሞ96 በመቶ ውጤታማነት አሳይቷል ብሏል ጥናቱ፡፡ እንደ ጥናቱ ከሆነ በኢትዮጵያ የመደበኛው ህክምና ውጤታማነቱ ከ55 በመቶ እንዲሁም በህንድ ከ88 በመቶ እንደማይበልጥ ጠቅሷል፡፡
የዲኤንዲ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ፋቢያማና አልቬዝ ሁለቱ በሽታዎች “አዲሱ የዓለም ጤና ድርጅት መመሪያ በሁለቱም በሽታዎች የተጠቁ፣ መገለልና መድሎ የደረሰባቸውን እና በገቢ ማጣት እንዲሁም በተደጋጋሚ የበሽታ ማገርሸት የሚሰቃዩትን ታካሚዎች ህይወት በእጅጉ የሚያሻሽል ጉልህ እርምጃ ነው።”
ጥናቱ በኤች አይ ቪ የተያዙ ሰዎች ከ100 እስከ 2,300 እጥፍ የሚደርስ ለቁንጭር (ካላዛር) በሽታ የመጋለጥ እድል እንዳላቸው አመልክቷል፡፡ የካላዛር በሽታ በአሸዋ ዝንብ ንክሻ የሚተላለፍ ነው፡፡
ድርጅቱ እንዳስታወቀው ከሆነ በትግበራ ላይ ያለው የሁለቱ በሽታዎች ህክምና (የሊፕሶማል) ህክምና የሚያካትት ሲሆን አዲሱ የህክምና ክትትል ደግሞ የአፍ ውስጥ ህክምና( ሚልትፎሲን) እና የሊፕሶማል አምፎትሪሲንን ያካትታል፡፡