መጨናነቅ ባለባቸው ቦታዎች አሽከርካሪዎችን በማስከፈል ኒው ዮርክ የመጀመሪያዋ የአሜሪካ ከተማ ሆነች
መጨናነቅ ባለባቸው ቦታዎች የሚያሽከርክሩ አሽከርካሪዎች 9 ዶላር ለመክፈል እንደሚገደዱ ተገልጿል
ባለፈው አመት ኒው ዮርክ ከተማ ለሁለተኛ አመት እጅግ የተጨናነቀች ከተማ ተብላ የትራፊክ እንቅስቃሴን በሚተነትነው አንሪክስ (INRIX) ተሰይማለች
የትራፊክ እንቅስቃሴ በተጨናነቀባቸው ቦታዎች በተሽከርካሪዎች ላይ የሚጣለው ክፍያ በኒው ዮርክ ከተማ ተግባራዊ ሆኗል።
መጨናነቅ ባለባቸው ቦታዎች የሚያሽከርክሩ አሽከርካሪዎች 9 ዶላር ለመክፈል እንደሚገደዱ ቢቢሲ ዘግቧል።
መጨናነቅ ያለበት ቦታ የኢምፓየር ስቴት ህንጻ፣ ታይም ስኩየርና በዋልስትሪት አካባቢ ያለውን ፋይናንሻል ዲስትሪክት የመሳሰሉ ታዋቂ ቦታዎች ያሉበትን የሴንትራል ፖርክ ደቡብ ክፍል የሚካትት ነው።
የአሜሪካዋ ኒው ዮርክ ከተማ የጦር መሣሪያ በአደባባይ እንዳይያዝ ከለከለች
አዲሱ አሰራር በአስቸጋሪነት የሚታወቀውን የኒው ዮርክ የትራፊክ ችግር ለማቀለል እና ለህዝብ ትራንስፖርት ኔትወርክ ብዙ ቢሊዮን ዶላሮች ለመሰብሰብ ያለመ ቢሆንም ከታዋቂ የኒው ዮርክ ነዋሪ ግለሰቦች እና ከተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጭምር ተቃውሞ ገጥሞታል።
የኒው ዮርክ ግዛት ገዥ ካቲ ሆቹል መጨናነቅ ባለባቸው አካባቢዎች አሽከርካሪዎች ክፍያ እንዲከፍሉ ሀሳብ ያቀረቡት ከሁለት አመት በፊት ሲሆን የተወሰኑ ተጠቃሚዎች እና የንግድ ተቋማት ያቀረቡትን ቅሬታ መነሻ በማድረግ እቅዱ እንዲዘገይ እና እንዲከለስ መደረጉ ተገልጿል።
አዲሱ እቅድ ባለፈው ሐምሌ ወር ያልተፈለገ ውጤት ሊያስከትል ይችላል በሚል የቆመውን መርሃግበር እንደገና የሚያስጀምር ነው።
አብዛኞቹ አሽከርካሪዎች መጨናነቅ ወደአለባቸው ቦታዎች ሲገቡ በቀን አንድ ጊዜ በስራ መውጫ እና መግቢያ ሰአት ወይም 'ረሽ ሀወር' 9 ዶላር በሌላ ጊዜ ደግሞ 2.25 ዶላር እንዲከፍሉ ይደረጋል።
አነስተኛ የጭነት መኪኖች እና የመንገደኛ ያልሆኑ አውቶብሶች ደግሞ በረሽ ሀወር ወደ ማንሀተን ሲገቡ 14.40 ዶላር ሲከፍሉ፣ ከባድ ተሽከርካሪዎች እና የቱሪስት መኪኖች ደግሞ 21.60 ዶላር ለመክፈል ይገደዳሉ ተብሏል።
ክፍያው ከታክሲ አሽከርካሪዎች ማህበር ጨምሮ ብዙ ተቃውሞ እየቀረበበት ነው። ነገርግን ከፍተኛ ተቃውሞ የመጣው ከኒው ዮርካዊው እና ቢሮ ሲገቡ መርሃግብሩን ውድቅ እንደሚያደርጉት ከዛቱት ከተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ነው።
የአካባቢው ሪፐብሊካን ሰዎች ትራምፕ ጣልቃ እንዲገቡ ጠይቀዋቸዋል።
ከኒው ዮርክ ከተማ ዳርቻ የምትገኘውን ዲስትሪክት የወከሉት ኮንግረስ ማን ማይክ ለውየር "ይህን የማይረባ ክፍያ" እንዲያስቆሙ ባለፈው ህዳር ወር ትራምፕን ጠይቀው ነበር።
ባለፈው አመት ኒው ዮርክ ከተማ ለሁለተኛ አመት እጅግ የተጨናነቀች ከተማ ተብላ የትራፊክ እንቅስቃሴን በሚተነትነው አንሪክስ (INRIX) ተሰይማለች