ሩሲያ የአሜሪካ ሰራሽ ሚሳይሎችን ማክሸፏን አስታወቀች
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ዩክሬን የረጅም ርቀት የአሜሪካ ሚሳይሎችን ተጠቅማ ሩሲያ ግዛት ውስጥ በመዝለቅ ጥቃት እንድትፈጽም ከፈቀዱላት ወዲህ ጥቃት እያደረሰች ነው
በጆ ባይደን ውሳኔ የተቆጣችው ሩሲያ ኦሬሽኒክ የተባለ አዲስ የመካከለኛ ርቀት ሚሳይል ወደ ዩክሬን ዲኒፕሮ ግዛት ማስወንጨፏ የሚታወስ ይታወሳል
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በምስራቅ ዩክሬን ሉሀንስክ ግዛት ናዲያ የተባለ መንድር መቆጣጠሯን እና ስምንት አሜሪካ ሰራሽ ኤቲኤሲኤምኤስ ሚሳይሎችን መትቶ ማክሸፉን በትናንትናው እለት አስታውቋል።
በተጨማሪም ሚኒስቴሩ የሩሲያ አየር መከላከያ 10 የዩክሬን ድሮኖችን በዩክሬን ግዛት ማውደሙን ገልጿል።
የሴንትፒተርስበርግ ከተማ ፑልኮቭ ኤየርፖርት የሚሰጠውን የበረራ አገለግሎት ትናንት ጠዋት አቋርጦ እንደነበር ዘገባው ጠቅሷል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ዩክሬን የረጅም ርቀት የአሜሪካ ሚሳይሎችን ተጠቅማ ሩሲያ ግዛት ውስጥ በመዝለቅ ጥቃት እንድትፈጽም ከፈቀዱላት ወዲህ ጥቃት እያደረሰች ነው።
በጆ ባይደን ውሳኔ የተቆጣችው ሩሲያ ኦሬሽኒክ የተባለ አዲስ የመካከለኛ ርቀት ሚሳይል ወደ ዩክሬን ዲኒፕሮ ግዛት ማስወንጨፏ የሚታወስ ይታወሳል።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ አዳዲስ ሚሳይሎችንም በውጊያው እንደሚጠቀሙ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።
አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን ወታደራዊ ድጋፍ ማድረጋቸውን ቢቀጥሉም፣ ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን ግስጋሴ እያደረገች ትገኛለች።
ሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነቱን እንዲቆም ያቀረባቸው ቅድመ ሁኔታዎች የተራራቁ ስለሆኑ ጦርነቱን በድርድር ለማስቆም የተደረገው ጥረት እስካሁን አልተሳካም።
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያ ዩክሬን- ጦርነትን እንደሚያስቆሙ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይደመጣሉ።
ትራምፕ ጦርነቱን ማስቆም የሚያስችል እቅድ እንዳላቸውና የእቅዱን ዝርዝር ይፋ ማድረግ እንደማይፈልጉ ከወራት በፊት መናገራቸው ይታወሳል።