ኒውዮርክ በትዳር አጋራቸው ላይ የማገጡ ሰዎችን የሚቀጣውን ህግ ልታነሳ ነው
የአሜሪካዋ ኒውዮርክ በትዳር አጋራቸው ላይ የማገጡ ሰዎችን በእስራት የሚያስቀጣ ህግ አላት
ኒውዮርክ በትዳር አጋራቸው ላይ የማገጡ ሰዎችን የሚቀጣ ህግ ከ1907 ጀምሮ ተግባራዊ አድርጋ ቆይታለች
የአሜሪካዋ ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ በትዳር አጋር ላይ መማገጥ በእስራት የሚያስቀጣ ህግ ከአንድ ምእተ ዓመት ባለይ ሲተገበር ቆይቷል።
ሆኖም ግን ከተማዋ በትዳር ላይ መማገጥን በቅርቡ ህጋዊ ልታደርግ ነው የተባለ ሲሆን፤ ይህም በትዳራቸው ላይ የማገጡ ሰዎችን እስከ 3 ወር በእስር የሚያስቀጣውን ህግ ሊያስቀር ይችላል ተብሏል።
በትዳር አጋራቸው ላይ የማገጡ ሰዎችን የሚቀጣውን ህግ በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ተጽፎ ቢገኝም፤ በዚህ ረገድ የሚመጡ ክሶች አነስተኛ መሆናቸው እና የቅጣት ፍርዶችም አልፎ አልፎ የሚተላለፉ መሆኑ ነው የሚነገረው።
ህጉ የወጣው በትዳር ላይ በመማገጥ ሳቢያ የሚከሰቱ ፍቺዎችን ለማቀረት ታስቦ እንደሆነም ነው የሚነገረው።
ይህ ህግ በአሜሪካዋ ኒው ዮርክ መተግበር የጀመረው በፈረንጆቹ 1907 ላይ ነው የተባለ ሲሆን፤ አንድ ባለትዳር ከትዳር አጋሩ ጋር እየኖረ ከሌላ ሰው ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ከፈጸመ የሚያስቀጣ ህግ ነው።
ህጉ ተግባራዊ እንደተደረገ በሳምንታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀጡትም አንድ በለትዳር ወንድ እና አንዲት 25 ዓመት ሴት ሲሆኑ፤ ሰዎቹ ለእስር ሊዳረጉ የቻሉትም ባሏ የማገጠባት ሚስት ፍቺ መጠየቋን ተከትሎ ነበር።
በፈረንጆቹ ከ1972 ጀምሮ በኒውዮርኩ ህግ የተከሰሱት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ናቸው የተባለ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ በአምስት ክሶች ላይ ብቻ የጥፋተኝነት ብይን መሰጠቱን ህጉ እንዲነሳ የጠየቁት የኒው ዮርክ ምክር ቤት አባል ቻርለስ ላቪን አስታውቀዋል።
በዚህ ህግ ስር ለመጨረሻ ጊዜ ክስ የቀረበው በፈረንጆቹ 2010 ላይ ሲሆን፤ ክሱም በህዝብ መናፈሻ ፓርክ ውስጥ ወሲባዊ ግንኙነት ስትፈጽም በተያዘች ሴት ላይ ነበር ተብሏል።
ምክር ቤት አባሉ ቻርለስ ላቪን፤ ህጉ በሚጠበቀው ደረጃ እየተተገበረ አይደልም፤ ስለዚህ አውጥን የምንጥለበት ጊዜ ደርሷል ሲሉም ተናግረዋል።
በኒው ዮርክ ህጉን ለማንሳት የቀረበው የውኔ ሀሳብ በከተመዋ ምክር ቤት የፀደቀ ሲሆን፤ ለኒውዮርክ አስተዳዳሪ ለፊርማ ከመቅረቡ በፊት ለሴኔት ቀርቦ ይወሰንበታልም ተብሏል።