የኒውዚላንድ ገበሬዎች ላሞቻቸው በሚለቁት ጋዝ ወይም “ፈስ” ግብር ትከፍላላችሁ መባሉን ተቃወሙ
የኒውዝላንድ መንግሥት በላም አርቢዎች ላይ አዲስ ግብር ጥሏል
መንግስት በገበሬዎቹ ላይ ግብር የጣለው ከላሞች በሚለቀቅ መጥፎ ሽታ ዜጎች ለአየር ብክለት ተጋልጠዋል በሚል ነው
የንድ ገበሬዎች ላሞቻቸው በሚለቁት ጋዝ ወይም “ፈስ” ግብር ትከፍላላችሁ መባሉን ተቃወሙ።
የእስያ ፓስፊኳ ኒውዝላንድ ወተት እና የወተት ተዋጽኦ ምርቶችን ወደ ተለያዩ የዓለማችን ሀገራት በመላክ ትታወቃለች።
እነዚህ ገበሬዎች በየጊዜው ወደ ተለያዩ የዓለማችን ሀገራት የእንስሳ ተዋጽኦዎችን በመላክ ኢኮኖሚዋን ትደጉማለች።
ይሁንና የኒውዝላንድ መንግስት ሰፋፊ የላም እርባታ የሚያካሄዱ አርብቶ አደሮች ላይ አዲስ የግብር ፖሊሲ አውጥታለች።
ይህ የግብር ፖሊሲ አርቢዎች ከላሞቻቸው በሚለቀቁ መጥፎ ሽታ ወይም ፈስ ምክንያት ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍሉ ያስገድዳል።
አዲሱን የግብር ፖሊሲ የተቃወሙ ገበሬዎች በኒውዝላድ ዋና ዋና መንገዶች ከነ ትራክተሮቻቸው በመውጣት የጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደን መንግስትን ተችተዋል ሲል አርቲ ዘግቧል።
በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተገኙ ላም አርቢዎች አዲሱ ግብር ከንግድ ስራቸው እንደሚያስወጣቸው እና በሌሎች ሀገራት ያሉ ደንበኞቻቸውን በዚህ ኢንቨስትመንት እንዲወጡ ያደርጋልም ብለዋል።
አርሶ አደሮቹ ላሞቻቸው የሚለቁትን መጥፎ ሽታ ያለው አየር ለማከም በየጊዜው ዛፎችን በመትከል ላይ እንደሆኑም ተናግረዋል።
ተቃውሞን እያስተናገደ ያለው የጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደን መንግስት እስካሁን ለተቃዋሚዎች ያለው ነገር የለም።