መስማት የማይችሉ ደጋፊዎች የፊታችን ቅዳሜ ኒውካስትል ከቶትንሀም ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ላይ እንደሚለብሱት ተገልጿል
መስማት ለማይችሉ የእግር ኳስ ደጋፊዎች ደስታን መጋራት የሚያስችል ልዩ ማልያ ተሰራ፡፡
የእንግሊዙ ኒውካስትል ዩናይትድ እግር ኳስ ክለብ መስማት ለተሳናቸው ደጋፊዎች የሚሆን ልዩ ማልያ ማሰራቱን አስታውቋል፡፡
ይህ ማልያ መስማት የተሳናቸው የክለቡ ደጋፊዎች በስታዲየም ውስጥ ያለውን የደጋፊዎች እና የእግር ኳስ ጨዋታ ድባብ በድምጽ እንዲያውቁት የሚደርግ መሆኑን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡
የፊታችን ቅዳሜ ኒውካስትል ዩናይትድ ከቶትንሀም ጋር በሚያደርገው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ መስማት የተሳናቸው ደጋፊዎች ማልያውን አድርገው ይገባሉ ተብሏል፡፡
በእግር ኳስ ጨዋታ አዲስ የተዋወቀው ሰማያዊ ካርድ ምንድን ነው?
ይህ ልዩ ማልያ በስታዲየሙ ሁሉም ስፍራዎች ላይ በሚገጠሙ ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት ማልያው በስታዲየሙ ውስጥ ያለውን ድባብ እና ስሜቱን ለሰው ልጅ በሚመጥን መልኩ እንዲያስተላልፍ ተደርጎ የተሰራ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ማልያውን ሰርቶ ለክለቡ ያስረከበው ኪውት ሰርኪውት የተባለው ኩባንያ እንዳለው ከሆነ ማልያውን መልበስ ማለት ስታዲየሙን መልበስ ማለት ነው ብሏል፡፡
በብሪታንያ 12 ሚሊዮን ህል ዜጎች መስማት የማይችሉ ወይም ለመስማት ይቸገራሉ የተባለ ሲሆን ይህ ቴክኖሎጂ የእግር ኳስ ደጋፊዎች የክለባቸውን ድባብ እንዲረዱ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡
ማልያውን የሰራው ይህ ኩባንያ ከዚህ በፊት የሙዚቃ ኮንሰርቶችን የሚሳተፉ መስማት የተሳናቸው ሰዎች ልዩ ቲሽርቶችን ለብሰው የተቀነባበሩ ወይም ክላሲካል ሙዚቃዎችን እንዲሰሙ ማድረግ ችሎ ነበር፡፡
ይህ ቴክኖሎጂ በፍራንሲስካ ሮሴላ እና ጓደኞቿ የተፈበረከ ሲሆን መስማት ለማይችሉ የማህበረሰብ አባላት ጥሩ እድል ይዘው ስለመምጣታቸው ተገልጿል፡፡