በእግር ኳስ ጨዋታ አዲስ የተዋወቀው ሰማያዊ ካርድ ምንድን ነው?
የአለም አቀፍ እግር ኳስ ማህበር ቦርድ ሰማያዊ ካርድ ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ ሰጥቷል
የእንግሊዝ የእግር ኳስ ማህበር ሰማያዊ ካርድ በ2024-25 ኤፍ.ኤ ዋንጫ ውድድር ላይ እንዲሞከር ፈቅዷል
የአለም አቀፍ እግር ኳስ ማህበር ቦርድ (አይ.ኤፍ.ኤ.ቢ) በእግር ኳስ ጨዋታ ወቅት ዳኞች ሰማያዊ ካርድ ጥቅም ላይ እንዲያውሉ ፈቃድ ሰጥቷል።
ሰማያዊ ካርድ ሆን ብለው ጥፋት ለሚፈፅሙ ተጫዋቾች እንዲሁም በጨዋታው ዳኛ ውሳኔዎች ላይ ያልተገባ ምላሽ ለሚያሳዩ ተጫዋቾች የሚሰጥ መሆኑንም ዘ ቴሌግራፍ አስንብቧል።
ሰማያዊ ካርዱ ቢጫ እና ቀይ ካርድ ወደ አገልግሎት ከገቡበት ከ1970 ወዲህ ዳኞች የሚጠቀሙበት የመጀመሪያው አዲስ ካርድ እንደሚሆንም ተነግሯል።
ሰማያዊ ካርድ ሆን ብለው ጥፋት ለሚፈፅሙ ተጫዋቾች እንዲሁም ለዳኛ ያልተገባ ባህሪ ለሚያሳዩ ተጫዋቾች የሚሰጥ ነው መሆኑም በሪፖርቱ ተመላቷል።
ሰማያዊ ካርድ የተመለከተ ተጫዋችም ለ10 ደቂቃ ያክል ከሜዳ ወጥቶ እንዲቆይ ከተደረገ በኋላ ተመልሶ ጨዋታውን እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው ተብሏል።
የአለም አቀፍ እግር ኳስ ማህበር ቦርድ (አይ.ኤፍ.ኤ.ቢ) ሰማያዊ ካርድ ላይ ሙከራ እንዲደረግ ባሳለፍነው ህዳር ወር ላይ ፈቃድ መስጠቱም ተነግሯል።
ይሁን እንጂ ይህ ነው የተባለ የሙከራ ጊዜ ያለተቆረጠለት ሲሆን፤ የእንግሊዝ የእግር ኳስ ማህበር በ2024-25 የወንዶች እና የሴቶች ኤፍ.ኤ ዋንጫ ውድድር ላይ እንዲሞከር ፈቅዷል።
አዲሱ ሰማያዊ ካርድ እንዴት ይሰራል?
ሰማያዊ ካርድ የተመለከተ ተጫዋች ለ10 ደቂቃ ያክል ከሜዳ ወጥቶ እንዲቆይ ከተደረገ በኋላ ተመልሶ ጨዋታውን እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው ተብሏል።
ሰማያዊ ካርዱ እና ከቢጫ ካርድ ጋር ተመሳሳይ አቅም እንዳላቸው የተገለጸ ሲሆን፤ በጨዋታ መካከል ሁለት ሰማያዊ ካርድ የተመለከተ ተጫዋች እንደ ሁለት ቢጫ ካርድ ተቆጥሮ ከሜዳ እንዲወጣ ይደረጋል ተብሏል።
እንዲሁም አንድ ሰማያዊ እና አንድ ቢጫ ካርድ የተመለከተ ተጫዋችም በድምር ቀይ ካርድ ተሰጥቶች ከጨዋታ እንዲወጣ ይደረጋልም ተብሏል።
ፊፋ ስለ አዲሱ ሰማዊ ካርድ ምን አለ?
ፊፋ 'ሰማያዊ ካርድ' እየተባለ የሚጠራው አዲሱ ካርድ ማጣርት እንደሚፈልግ እና የእግር ኳስ ደረጃ የተሳሳቱ እና ያለጊዜው የተከሰተ ነው ሲል አጣጥሎታል።
ይሀ ካርድ የሚሞከር ከሆነም በዝቅተኛ ደረጃ በሚገኙ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ የተገደበ መሆን እንደሚገባው እና ሙከራውም ኃፊነት በተሞላበት ሊደረግ እንደሚገባ አሳስቧል።