የኔይማሩ አል-ሂላል በተከታታይ በማሸነፍ አዲስ ሪከርድ አስመዘገበ
ግዙፉ የሳኡዲ ክለብ ባደረጋቸው 21 ጨዋታዎች 59 ነጥቦችን በመሰብሰብ በሰባት ነጥብ ልዩነት በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አንደኛ ላይ ተቀምጧል
አል-ሂላል አል-ኢቲፋቅን 2-0 በማሸነፍ፣ በሳኡዲ ፕሮሊግ በተከታታይ ድል በማድረግ አዲስ ሪከርድ አስመዝግቧል
የኔይማሩ አል-ሂላል በተከታታይ በማሸነፍ በሳኡዲ ፕሮሊግ አዲስ ሪከርድ አስመዝግቧል።
አል-ሂላል በትናንትናው እለት አስተናጋጁን አል-ኢቲፋቅን 2-0 በማሸነፍ፣ በሳኡዲ ፕሮሊግ በተከታታይ ድል በማድረግ አዲስ ሪከርድ አስመዝግቧል።
ግዙፉ የሳኡዲ ክለብ ባደረጋቸው 21 ጨዋታዎች 59 ነጥቦችን በመሰብሰባ የክሪስቲያኖ ሮማልዶውን አልናስርን በሰባት ነጥብ በልጦ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አንደኛ ላይ ተቀምጧል።
አሰልጣኝ ጆርጅ ጀሲዩስ በሊጉ ለ14 ተከታታይ ጊዜ በማሸነፍ፣ አል-ናስር ከፈረንጆቹ 2013-2014 ለተከታታይ 13 ጊዜ በማሸነፍ ይዞት የነበረውን ሪከርድ ሊሰብር ችሏል።
በዚህ ጨዋታ ሰርጌ ሚሊኒኮቪክ ሳቫክ ከማዕዘን የተሻገረችለትን ኳስ በ40ኛው ደቂቃ ወደ ግብ በመቀየር አል-ሂላል እንዲመራ አስችሎታል። ሳሌም አል ዳውሳሪ ደግሞ በመጀመሪያ የጨዋታ አጋማሽ ጭማሪ ደቂቃ ሁለተኛዋን ግብ አስቆጥሯል።
ኮከብ ግብ አስቅጣሪ አሌክሳንደር ሚትሮቪክ ቢጫ ካርድ ባያይ ኖሮ የአል-ሂላል ምሽት ፍጹም አሪፍ ይሆን ነበር።
ተጨዋቹ ባለው የካርድ ክምችት ምክንያት አል-ሂላል ከባለፈው አሸነፊ አሊ-ትሀድ ጋር በቀጣይ በሚያደርገው ጨዋታ አይሳተፍም።
በአውሮፖ ክለቦች ይጫወቱ የነበሩ ሰመ ገናና ተጨዋቾች የሳኡዲ አረቢያውን ፕሮ ሊግ መቀላቀላቸው የሊጉን ደረጃ ከፍ አድርጎታል። ባለፈው ነሀሴ ወር አል-ሂላልን የተቀላቀለው ብራዚላዊው አጥቂ ኔይማር ፕሮሊግን ከተቀላቀሉ ታዋቂ ተጨዋቾች አንዱ ነው።