ኔይማርን ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለፈው አል ሂላል ተቀናቃኙን 6-1 አሸነፈ
የብራዚል ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የፔሌን ክብረወሰን የሰበረው ኔማር ባጋጠው የተረከዝ ጉዳት ምክንያት ወደ ሳኡዲ አረቢያ ከተዛወረ ወዲህ ለአል ሂላል አልተጫወተም ነበር
ባለፈው ወር በ90 ሚሊዮን ዩሮ ከፒኤስፒ ለአል ሂላል የፈረመዉ የ31 አመቱ ተጨዋች የአል ሂላል አራኛው ግብ በ83 ደቂቃ እንዲቆጠር ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል
ኔይማርን ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለፈው አል ሂላል አል ሪያድን 6-1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የሳኡዲ ፕሮ ሊጉ አልሂላል ተቀናቃኙን አልሪያድን 6-1 ባሸነፈበት ጨዋታ የብራዚሉ የምንግዜም መሪ ግብ አስቆጣሪ በ26ኛው ደቂቃ በመግባት ለክለቡ ለመጀመሪያ ጊዜ መጫወቱን ሮይተርስ ዘግቧል።
ባለፈው ወር በ90 ሚሊዮን ዩሮ ከፈረንሳይ ፖሪስ ሴንት ጄርሜን(ፒኤስፒ) ለአል ሂላል የፈረመዉ የ31 አመቱ ተጨዋች የአል ሂላል አራኛው ግብ በ83 ደቂቃ እንዲቆጠር ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል።
አል ሂላል በያሲር አልሻህራኒ እና ናስር አል ዳውሳሪ ጎሎች ተጨማሪ ጎሎች ከመምራቱ በፊት በ30ኛው ደቂቃ ነበር አሌክሳንደር ሚትሮቪች የመጀመሪያውን ግብ ያስቆጠረው።
የብራዚል ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የፔሌን ክብረወሰን የሰበረው ኔማር ባጋጠው የተረከዝ ጉዳት ምክንያት ወደ ሳኡዲ አረቢያ ከተዛወረ ወዲህ ለአል ሂላል አልተጫወተም ነበር።
የሳኡዲ አረቢያ ፕሮ ሊግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የገነነ ሰም ያላቸው በአውሮፖ ሊግ የሚጫወቱ ተጨዋቾች ምርጫቸው እየሆነ መጥቷል።
ሳኡዲ አረቢያም በተጠናቀቀው የግማሽ አመት ለተጨዋቾች ዝውውር ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገደማ ወጭ በማድረግ በእስያ እግር ኳስ ትልቅ ድርሻ ይዛለች።