ጥያቄው የቀረበው በአፍሪካ እየተስፋፋ የመጣው የጽንፈኞች ጥቃት እየተባባሰ በመምጣቱ ነው ተብሏል
የናጀሪያው ፕሬዘዳንት ሙሀመዶ ቡሀሪ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተዮኒ ብሊከን ጋር የቪዲዮ ውይይት አደርገዋል።
ፕሬዘዳንቱ በውይይቱ ላይ አሜሪካ በጀርመኗ ስቱትጋርት ከተማ ዋና መቀመጫውን ያደረገው የአፍሪካ ዋና እዝ (አፍሪኮም) ወደ አፍሪካ እንድታዞር ጠይቀዋል።
ሁለቱ መሪዎች በአፍሪካ በተለይም በምዕራብ እና ማዕከላዊ አፍሪካ አገራት እየተስፋፋ ያለው የጽንፈኞች ጥቃት እና አለመረጋጋት እልባት እንዲያገኝ አሜሪካ ድጋፍ እንድታደርግ ጠይቃዋል።
ፕሬዘዳነት ቡሀሪ ናይጀሪያ በምዕራብ አፍሪካ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ መሆናቸውን አክለው አሜሪካም ድጋፍ እንድታደርግ መጠየቃቸውን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።
መሪዎቹ ከዚህ ባለፈም በናይጀሪያ-አሜሪካ የሁለትዮሽ ወዳጅነት ዙሪያ መወያየታቸው የተገለጸ ሲሆን በተለይም የናይጀሪያ ኢኮኖሚ ከኮሮና ቫይረስ ጉዳት ስለሚያገግምበት ስለ አየር ንብረት ለውጥ እና በሌሎች አጀንዳዎች መወያየታቸው ተገልጿል።