በናይጀሪያ “ከ1,800 በላይ የሚሆኑት ታራሚዎች ከወህኒ ቤት”አመለጡ ተባለ
ፖሊስ ለጥቃቱ ተገንጣይ ቡዱን የሚላቸውን “የቤያፍራ ተወላጆች” ተጠያቂ አድረግዋል
ከጥር ወር ወዲህ በርካታ የናይጄሪያ ፖሊስ ጣቢያዎች ጥቃት እየደረሰባቸው ይገኛል
እስረኞቹ ከወህኒ ቤት ያመለጡት ሮኬት፣ በራሪ ቦምብ ፣ መትረየስ ፣ ፈንጂ እና ጠመንጃ የያዙ ታጣቂዎች ጥቃት ማድረሳቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ታጣቂዎቹ ከናይጄሪያ ትልቁ ከተማ ሌጎስ በስተደቡብ ምስራቅ 400 ኪ.ሜ (260 ማይል) ርቀት በምትገኘው ኦወሪ ከተማ ፤በሚገኘው የማረሚያ ቤቱ አስተዳደራዊ ስፍራ ላይ ፍንዳታ በማካሄድ ወደ ወህኒ ቤቱ ቅጥር ግቢ ለመግባት ፈንጂዎችን መጠቀማቸውንም ነው ሮይተርስ የዘገበው፡፡
የናይጄሪያ ማረሚያ አገልግሎት ሰኞ ማለዳ ከጥቃቱ በኋላ 1 ሺህ 844 እስረኞች ማምለጣቸውን አረጋግጧል፡፡
የናይጄሪያ ፖሊስ ጥቃቱን “የቤያፍራ ተወላጆች” ስበስብ እንደሆነ በሚነገርለትና በታገደው ተገንጣይ ቡድን ተፈፅመዋል ሲል ቡዱኑን ተጠያቂ አድርጓል፡፡
ፖሊስ ተገንጣይ ያለው ቡዱን ተጠያቂ ቢያደርግም፤ ቡዱኑ ግን ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ኃላፊነት እንደማይወስድ መግለፁን የፈረንሳዩ የዜና ወኪል/ኤ.ኤፍ.ፒ) ዘግበዋል፡፡
ምንም እንኳን አስካሁን ኃላፊነት የወሰደ አካል ባይኖርም፤ ከጥር ወር ወዲህ በርካታ የደቡብ ምስራቅ ናይጄሪያ ፖሊስ ጣቢያዎች ጥቃት ማስተናገዳቸውና በዚህም ከፍተኛ መጠን ያላቸው ጥይቶችም መዘረፋቸው የሚታወቅ ነው፡፡