በናይጄሪያ 162 ሺህ ሰዎች ላይ ኮቪድ 19 ሲገኝ፤ 2 ሺህ 31 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸውን አጥተዋል
የናይጄሪያ ተመራማሪዎች ሁለት የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባቶችን ማግኘታቸውን የሀገሪቱ መንግስት አስታወቀ።
የናይጄሪያ መንግስት ቃል አቀባይ እና የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ያቋቋሙት የኮቪድ 19 ግብረ ኃይል ሰብሳቢ ቦስ ሙስጠፋ፥ በአሁኑ ወቅት በክትባቶቹ ላይ ክሊኒካል ሙከራዎች እየተደረጉ ነው ማለታቸውን ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል።
ክትባቶቹ የክሊኒካል ሙከራዎችን በማጠናቀቅ የእውቅና የምስክር ወረቀት ሲያገኙ ጥቅም ላይ መዋል ይጀምራሉ ብለዋል።
የክትባቶቹ መገኘት በናይጄሪያ የህክምና ኢንዱስትሪ ውስጥ አዲስ ተስፋን ይዞ የሚመጣ መሆኑንም ቦስ ሙስጠፋ ተናረዋል።
በናይጄሪያ እስካሁን 162 ሺህ ሰዎች ላይ ኮቪድ 19 ቫይረስ የተገኘ ሲሆን፥ 2 ሺህ 31 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸውን አጥተዋል።