በዓለምጤና ድርጅትና አጋሮቹ የሚመራው ኮቫክስ ለ20 ሀገራት የኮሮና ክትባት አከፋፈለ
ኮቫክስ በፈረንጆቹ 2021፣ ሁለት ቢሊዮን ክትባት ለማሰራጨት አልሟል
የዓለም ጤና ድርጅት በመጭው ሳምንት ለተጨማሪ 31 ሀገራት ክትባት እንደሚያሰራጭ አስታውቋል
የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር እንዳስታወቁት በአለምጤና ድርጅትና በአጋሮቹ የሚመራው ኮቫክስ 20 ሚሊዮን የኮሮና ክትባቶችን ለ20 ሀገራት ማድረሱን አስታውቀዋል፡፡
በዚህ ሳምንት የመጀመሪያው በአፍሪካ የኮሮና ክትባት ማዳረስ ዘመቻ በኮቫክስ በኩል ወደ ጋናና ኮትዲቮር የደረሲ ሲሆን ቀጥሎ አብዛኞች አፍሪካዊ ለሆኑ 18 ሀገራት ይሰራጫል፡፡ በመጭው ሳምንት ኮቫክስ 14.4 ሚሊዮን የሚሆኑ ክትባቶችን ለተጨማሪ 31 ሀገራት እንደሚዳረስ የድርጅቱ ዳይሬክር ቴድሮስ አድሃኖም በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
ነገርግን በኮቫክስ በኩል እየተሰራጨ ያለው የክትባት መጠን በአንጻራዊነት ትንሽ ነው፤ የተሰራጨው ክትባት በኮቫክስ ከ2 እስከ 3 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ይሸፍናል ተብሏል፡፡ ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ ክትባት አምራቾችን የማምረት አቅም ካላቸው ድርጅቶች ጋር ለማገናኘት እየጣሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዳይሬክተሩ የኮሮና ክትባትን በባለቤትንት የያዙ ሰዎች ማምረት ለሚችሉ ድርጅቶች አሳልፈው እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ባለቤትነትን በማስተላለፍ በድርጅቱ እንደ ጥሩ ምሳሌ የተቀመጠው አስተራዘኔካ ነው፤ ምክንያቱም አስትራዜኔካ ቴክኖሎጅውን በኮሪያ ለሚገኘው ኤስኬባዮና ለህንዱ ሴረም ኢንስቲትዩት አስተላልፏል፡፡ ኮቫክስ በፈረንጆቹ 2021፣ ሁለት ቢሊዮን ክትባት ለማሰራጨት አልሟል፡፡