የቦኮ ሃራም የሽብር ቡድን መሪ ክፉኛ መቁሰሉ ተሰማ
መሪው አቡ በከር ቼኩይ አይ.ኤስ.አይ.ኤስ በቁጥጥር ስር ሊያውለው ሲል ራሱን ሲከላከል ነው የቆሰለው
የቦኮ ሃራም መሪ አቡ በከር ቼኩይና ሌሎች የቡድኑ አባላት ከአይ.ኤስ.አይ.ኤስ ጋር በትናትናው እለት መዋጋታቸው ተነግሯል
በናይጄሪያ የሚንቀሳቀሰው የቦኮ ሃራም የሽብር ቡድን መሪ አቡ በከር ቼኩይ ክፉኛ መቁሰሉ ተሰምቷል።
የሽብር ቡድኑ መሪ አቡ በከር ቼኩይ የሽብር ቡድን የሆነው አይ.ኤስ.አይ.ኤስ ቡድን በቁጥጥር ስር ሊያውለው ሲል ራሱን ሲከላከል መቁሰሉ ተሰምቷል።
የሽብር ቡድን የሆነው አይ.ኤስ.አይ.ኤስ በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ የቦኮ ሃራም መሪን በቁጥጥር ሰር ሊያውል እንደነበረ ተሰምቷል።
ይህ ይፋ የተደረገውም ደህንነት አባል የሆኑ ሁለት የመረጃ ምንጮች ለኤ.ኤፍ.ፒ በሰጡት መረጃ መሆኑም ታውቋል።
የመረጃ ምንጮቹ እንደሚናገሩት፤ “የቦኮ ሃራም መሪ አቡ በከር ቼኩይ እና ሌሎች የቡድኑ አባላት ከአይ.ኤስ.አይ.ኤስ ጋር ከተዋጉ በኋላ በትናትናው እለት በሳምቢሳ ጫካ ውስጥ ነው የተከበቡት”።
“የቦኮ ሃራም መሪ አቡ በከር ቼኩይ በዚሁ ወቀት በአይ.ኤስ.አይ.ኤስ ላለመያዝ ሲል ራሱ ላይ ተኩሶ ደረቱ ላይ ቆስሏል” ብሏል አንደኛው የመረጃ ምንጭ።
ሌላኛው የመረጃ ምንጭ ደግሞ አቡ በከር ቼኩይ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በታሰሩበት ቤት ውስጥ ራሱ ላይ ባፈነዳው ቦምብ መቁሰሉን የሚያሳይ ነው።
በርካታ የቦኮ ሀራም ተዋጊዎች ቡድኑን መሪ አቡ በከር ቼኩይን ይዘው ከስፍራው ለቀው ለመሄድ ማቀዳቸውንም የመረጃ ምንጮቹ ተናገረዋል።