በፈረንጆቹ 2009 እንቅስቃሴ የጀመረው ቦኮ ሀራም እስካሁን 30ሺ ሰዎችን ገድሏል
በፈረንጆቹ 2009 እንቅስቃሴ የጀመረው ቦኮ ሀራም እስካሁን 30ሺ ሰዎችን ገድሏል
የናይጀሪያ ወታደሮች 16 የቦኮሃራም ሽብር ቡድን አባላትን በሰሜን ምስራቅ መግደላቸውን የጦሩ ከፍተኛ ባለስልጣን አስታውቀዋል፡፡
ሲጂቲኤን እንደዘገበው እነዚህ አሸባሪዎች ሲገደሉ ሌሎች በተደረገው ዘመቻ የቆሰሉ ሲሆን ማምለጥ መቻላቸውን ዘግቧል፡፡ ባለስልጣኑ 11 አሸባሪዎች ከነመሳሪያቸው መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡
ደምአፋሳሽ ሆነውን ተግባር በፈረንጆቹ 2009 ጀመረ ቢሆንም ቆይቶ ይህ የግፍ ስራ ኒጀር፣ ቻድና ካሜሩን በመዛመቱ ምክንያት ወታደራዊ ምላሽ እንዲቋቋም አስገድዷል፡፡ እንደ ተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት አስተባባሪ ቦኮሀራም በናይጀሪያ ጥቃት ከጀመረ ጀምሮ 30 ሺ የተገደለ ሲሆን 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ተፈናቅለዋል፡፡
እንደ ተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ ቦኮሀራም በቻድ ሀይቅ አካባቢ የሚገኙ 26 ሚሊዮን ሰዎችን አጥቅቷል፤ 2.6 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ እንዲፈናቀሉ አድርጓል፡፡