ናይጀሪያ ከትዊትር ኃላፊዎች ጋር ከተወያየች በኋላ በትዊተር ላይ ጥላ የነበረው እግድ ልታነሳ ነው
ትዊተር በናይጀሪያ እግድ የተጣለበት ከ2 ወራት በፊት ነበር
ናይጀሪያ በትዊተር ላይ እግድ የጣለቸው ትዊተር የፕሬዘዳንት ሞሃመድ ሁሃሪን የትዊተር መልእክት መሰረዙን ተከትሎ ነበር
ናይጀሪያ ግዙፍ ከሆነው የትዊተር ኃላፋች ጋር ያላትን ልዩነት ከፈታች በኋላ ሀገሪቱ በትዊተር ላይ ጥላው የነበረውን እግድ ልታነሳ መሆኑን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ ላአይ ሞሃመድ ተናግረዋል፡፡
የፌደራል መንግስት ከሁለት ወር በፊት እግድ የተጣለበት ትዊትር እግዱ እንደሚነሳላት ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ እግድ የሚነሳው በመንግስት እና የትዊተር ኃለፊዎች በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት ከፈቱ ኃላ ነው፡፡
የናይጀሪያ መንግስት ባለፈው ሰኔ ወር ትዊተር የናይጀሪያ ፕሬዘዳንት ሞሃመድ ቡሃሪ የጻፉት የትዊተር መልእክት ከሰረዘ በኋላ ነበር በሀገሪቱ እንዳይሰራ ላልተወሰነ ጊዜ የታገደው፡፡ትዊተር የተሳሳተ መረጃ በሚዘዋወርባትና ሃሰተኛ መረጃ እየተሳፋፋ ባለባት ናይጀሪያ ፕሬዘዳንቱ የጻፉት መልእክት ግጭት የሚቀሰቅስና ተገቢ ባለመሆኑ መሰረዙን ትዊተር በጊዜው ገልጾ ነበር፡፡
ሚኒስትሩ ከትዊተር ኃላፊዎች ጋር ተከታታይ ውይይት ከተካሄደ በኋላ ችግሩ መፈታቱን ለጋዜጠኖች ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትሯ ትዊተር ድጋሚ ስራውን እንዲሰራ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች መኖራቸውንና ስምምነት እንደተደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡
ትዊተር በናይጀሪያ ቢሮ ይክፈትና የስታፍ ሰራተኞች ይኑሩት የሚለው ጉዳይ እስካሁን በውይይት ላይ ያለና ያያቀ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡