ናይጄሪያ ፌስቡክን ጨምሮ ሌሎች የመገናኛ ዘዴዎች የጥላቻ ንግግሮችን እንዲቆጣጠሩ አሳሰበች
የናይጄሪያ ማስታወቂያ ሚኒስትር “የቢያፍራ ተወላጆችን ፌስቡክ በመጠቀም ጥላቻ ንግግር እያሰራጩ ነው” ብሏል
ናይጄሪያ በጥር ወር በትዊተር ላይ የጣለችው የስድስት ወራት እገዳ ማንሳቷ ይታወሳል
ናይጄሪያ ፌስቡክን ጨምሮ ሌሎች የመገናኛ ዘዴዎች የጥላቻ ንግግሮች እንዲቆጣጠሩ አሳሰበ፡፡
የናይጄሪያ ማስታወቂያ ሚኒስትር መሀመድ እንዳስታወቁት ሀገሪቱ የማህበራዊ ሚዲያ ኃላፊነት የተሞላበት የመጠቀም ዘመቻ እያጠናከረች ባለችበት ወቅት፤ ፌስቡክን እና ሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በድረገጻቸው ላይ የጥላቻ ንግግሮችን ለመቆጣጠር የሚያደርጉት ጥረት ውስን ነው ሲሉ ወቅሷል፡፡
ሚኒስትሩ ይህን ያሉት፤ በሀገሪቱ የቢያፍራ ተገንጣይ ቡዱን አባላት በማህበራዊ ሚዲያዎችና ድህረገጾች ላይ የሚያሰራጫዋቸውን የጥላቻ ንግግሮችን በማስመለከት፤ በናይጄሪያ ዋና ከተማ አቡጃ ከፌስቡክ ኩባንያ ተወካዮች ጋር ከተወያዩ በኋላ መሆኑም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ሚኒስትሩ “ናይጄሪያ ለፌስቡክ ኩባንያ ብዙ ቅሬታዎች ብታቀርብም የቢያፍራ ተወላጆች በፌስቡክ የሚያሰራጩት የጥላቻ ንግግር ለመግታት ምንም አላደረገም” ብሏል።
ተገንጣይ ቡድኑ በአሸባሪነት መፈረጁን የገለጹት ሚኒሰትሩ፤ ፌስቡክ ቡዱኑ የጀመረውን የጥላቻ እና ሀገሪቱን የማተራመስ ዘመቻ ፌስቡክ እንደዋና መሳሪያ አድረጎ ሊጠቀምበት አይገባም ሲሉም ለኩባንያው ተወካዮች ጠይቋል፡፡
ሚኒስትሩ፤ መንግስት ናይጄሪያውያን የማህበራዊ ሚዲያን እንዳይጠቀሙ የመከልከል ዓላማ እንደሌለውና ዜጎች በኃላፊነት እንዲጠቀሙ የሚያበረታታ መሆኑም ገልጿል፡፡
ናይጄሪያ በጥር ወር በትዊተር ላይ የጣለችው የስድስት ወራት እገዳ ማንሳቷ አይዘነጋም፡፡
የትዊተር ኩባንያ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ሙሐመዱ ቡሃሪ የጻፉትን በማጥፋቱ ምክንያት መተግበሪያው በሀገሪቱ እንዳይሰራ ታግዶ ነበር።
ትዊተር የፕሬዝዳንቱን ጹሁፍ ያጠፋው ህጉን እንደሚጥስ በመጥቀስ መሆኑን ተከትሎ ነበር።
የናይጄሪያ መንግስት ቃል አቀባይ ፕሬዝዳንቱ ሃሳባቸውን የመግለጽ መብት እንዳላቸው ገልጾ ትዊተር ትክክል ያልሆነ ስራ ነው የሰራው ብሎ ነበር።
የሌጎስ የንግድና ኢንዱስትሪ ማህበራት በወቅቱ እንዳስታወቀው፤ በሰባት ወራት ውስጥ ትዊተር ስራ ላይ ባለመቆየቱ በሀገሪቱ ላይ የ26 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ወይም የ 10 ነጥብ 72 ትሪሊዮን የናጄሪያ ናይራ ኪሳራ መድረሱን ገልጿል።