90 በመቶ ያህሉ የአፍሪካ ቅርሶች በአውሮፓ እንደሚገኙ ይነገራል
እንግሊዝ ከ100 ዓመት በፊት ከናይጀሪያ የዘረፈቻቸውን ቅርሶችን መለሰች።
የእንግሊዝ ጦር ከ100 ዓመት በፊት ከናይጀሪያዋ ቤኒን ከተማ የዘረፋቸውን ሁለት የመዳብ ቅርሶች መመለሱ ተገልጿል።
ቅርሶቹ ከቤኒን ከተማ ተዘርፈው ከተወሰዱ በኋላ ወደ እንግሊዝ ተወስደው በብሪቲሽ ሙዚየም ውስጥ ቆይተዋል ተብሏል።
የቀድሞ ቤኒን ስርወ መንግስት በአሁኑ ወቅት በደቡብ ምዕራብ ናይጀሪያ የምትገኘው ቤኒን ከተማ እነዚህ ቅርሶች ቀድመው ይገኙበት ወደ ነበረው ቤኒን ባህላዊ ቤተ መንግስት መመለሳቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የቤኒን ከለተማ ከ100 ዓመት በፊት የተዘረፉባት ሁለት የመዳብ ቅርሶቿን በትናንትናው እለት ተረክባለች።
የብሪታኒያ መንግስት ቅርሶቹን ለናይጀሪያ ለመመለስ ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ላይ በተናገረው መሰረት ትናንት ቅርሶቹ ወደተዘረፉበት ስፍራ ደርሷል።
በርካታ የአፍሪካ አገራ በቅኝ ግዛት ጊዜ በአውሮፓዊያን የተዘረፉባቸውን ቅርሶች ለማስመለስ በጥረት ላይ ይገኛሉ።
90 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ ቅርሶች አሁንም በአውሮፓ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን ፈረንሳይ እና እንግሊዝ ደግሞ በአንጻራዊነት ብዙ የአፍሪካ ቅርሶች የሚገኙባቸው አገራት ናቸው።
በፈረንሳይ በሚገኝ አንድ ሙዚየም ውስጥ ብቻ 70 ሺህ የአፍሪካ ቅርሶች እንደሚገኙበት ዘገባው አክሏል።